አንጀሊና ጆሊ ከብራድ ፒት ጋር በ2024 ከተፋቱ በኋላ ምንም ዓይነት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንዳልገባች ገለፀች
ለተዋናይቷ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደገለጹት፣ ጆሊ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ስድስት ልጆቿን በማሳደግ ላይ አድርጋለች።
"ለእሷ አዲስ የፍቅር ግንኙነት ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ አይደለም፤ ይልቁንም ልጆቿ ደስተኛና ስኬታማ መሆናቸውን ማረጋገጥ ትፈልጋለች" ሲል ምንጩ ለፒፕል መጽሔት ተናግሯል።
አንጀሊና ጆሊ በቅርቡ "Couture" የተሰኘ አዲስ ፊልም ለዕይታ ያበቃች ሲሆን፣ በፊልሙ ላይ የጡት ካንሰርንና ፍቺን የምትጋፈጥ አንዲት ዳይሬክተር ሆና ትተውነዋለች።
ይህ ፊልም ለእሷ የግል ታሪኳን የሚገልጽ መሆኑን ጠቅሳለች። ከዚህ በመቀጠልም "Anxious People" በተሰኘ ተከታታይ ድራማ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅቷን ጨርሳለች።

5 months ago