ወላይታ ዞንን ውበት ያላበሰው የሞቼና ቦራጎ ዋሻ
#ethiopia | 500 ሰዎችን ማኖር የሚችለው አስገራሚው ዋሻ በወላይታ ዞን የሚገኘው ሞቼና ቦራጎ ዋሻ
በውስጡ 500 ሰዎችን ማኖር የሚችል በወላይታ ሶዶ የሚገኘው አስገራሚው የሞቼና ቦራጎ ዋሻ
ሞቼና ቦራጎ ዋሻ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ዳሞታ ተራራ ስር የሚገኝ እጅግ አስገራሚ ዋሻ ነው፡፡
ዋሻው ከሶዶ ከተማ በሆሳና - አዲስ አበባ በኩል ከዋናው መንገድ በስተቀኝ በኩል በ 12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ከባህር ወለል በላይ በ 2 ሺህ 340 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ነው፡፡
የዋሻው ጣሪያ 33 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን 50 ሜትር ስፋት አለው፡፡
በዓለም የበረዶ ዘመን ተብሎ በሚጠራው አስቸጋሪ ዘመን የሰው ልጅ ሕይወትን የታዳገ ዋሻ እንደነበርም ታሪክ ያስረዳል።
ከፈረንሳይ እና ከጀርመን በመጡ አርኪኦሎጂስቶች በተደረገው ጥናት መሠረት በዓለም የበረዶ ዘመን ወቅት የሰው ልጅ በዋሻው የተንሰራራበት ስፍራ እንደሆነም ይገለፃል።
የዋሻው ግድግዳ ተፈጥሯዊ በሆኑ ዓለቶች የተገነባ ሲሆን ከአሜሪካ፣ ከፈረንሣይ እና ከጀርመን በመጡ አርኪኦሎጂስቶች በተካሄደው የአርኪኦሎጂ ቁፋሮ የሰው ልጅ በዋሻው ውስጥ ከ 58 ሺህ እስከ 70 ሺህ ዓመታት በፊት ይኖር እንደነበር ያሳያል ተብሏል፡፡
ሞቼና ቦራጎ ዋሻ 500 ሰው አንደላቆ ማኖር የሚችል ሰፊ ዋሻ ነው።
በተደረጉ ጥናቶች ቦቼና ቦራጎ ዋሻ የሰው ልጆች በዓለም የበረዶ ዘመን ወቅት ተጠልለው ያሳለፉበትና የተሳካ ፍልሰት ከተከናወነባቸው የዓለም 7 ቦታዎች መካከልም አንዱ ነው።
የሰው ልጅ የተረጋጋ ኑሮ የጀመረበት፣ ምግብ አብስሎ የተመገበበት፣ ልብስ ሸምኖ የለበሰበት ጥንታዊ ስፍራ ሲሆን፤ ለዚህም መገለጫ የሆኑ የተለያዩ የመገልገያ ቁሳቁሶች በዋሻው ይገኛሉ።
በጥናት የተገኙ ቁሳቁሶችም ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለሥልጣን የተረከቡ መሆኑንም መረጃዎች ያመለክታሉ።
ዳሞት ተራራ የያዘው ታሪክ ምን ይመስላል?
የወላይታ ዳሞት ተራራ ብርቅና ድንቅ የቱሪስት መስህቦችን እና ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸው ቅርሶች ያቀፈ ተራራ ነው።
የዳሞት ተራራ ስያሜ የሚነሳው ጥንታዊ የዳሞት መንግስት እና የህዝቦቿ ታሪክ መነሻ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ይገልፃሉ።
የዳሞት ኪንግደም ወይም ወላይታ መንግስት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ግማሽ ክፍል ሲገዛ በወቅቱ ንጉሥ ሳሶ ሞቶሎቄን ጨምሮ ንጉሥ ሳቶ ሞቶሎሚ ኃያልነት የሚነሳው ከወላይታ ዳሞት ይነሳል።
የዳሞት መንግስት በወቅቱ ከፍተኛ የፈረስ እና እግረኛ ጦር የነበረው እና ከኬንያ ቱርካና ሀይቅ ጀምሮ እስከ ቡልጋ ሕትሳ ወይም ፅላልሽ ዘወረረ ድረስ እንዲሁም እስከ ዤማ ወንዝን አጠቃሎ የአባይና አዋሽ ተፋሰስን በስሩ ይዞ ያስተዳድር እንደነበር የታሪክ መረጃ እስከ ትውልድ ተሻግረዋል።
የዳሞት ተራራ ታሪካዊነት ሲነሳ በ1270 ዓ.ም ንጉሥ ሞቶሎሚ የአቡነ ተክለሃይማኖት ስብከት ተቀብለው 10,999 ሰዎች ጋር በወላይታ ለመጀመሪያ ጊዜ በቁጥር ብዙ ሰዎች በአንድ ቀን ክርስትና እምነት የተቀበሉት ወይም የተጠመቁበት ምንጭ ውሃ ያለበት ሥፍራ ሲሆን የንጉሥ ሞቶሎሚ ጥምቀት ቦታ በአካባቢው መጠሪያ "ዎሶሊ ፑልቱዋ"እየተባለ እስካሁን ይገኛል።
የወላይታማላ ሥርዎመንግስት ዘመን የሞቶሎሚ ቤተመንግሥት ያለበት "ጣዛ ጋሩዋ"ን ጨምሮ በርካታ ታሪካዊ ሥፍራዎች ያሉበት ነው ዳሞት ተራራ።
ከእነዚህም ለአብነት "ጦሳ ፔንጊያ ፤ኪኬ ዳሞታ፤ ቆሊ ቦርኮታ፤ ሀዴ ግታ፤ ቄንእቀንኣ፤ ፓራንቲያ ፤ዳጌቾ፤ ቦቄና ሶዶ፤ ዋንዳራ ጦማ ገራ፤ ሌራቶ ጎዳ ቡልኪያ፤ ዎጋ አንታሺያ፤ ዎጋ ኮካ፤ ቀሪ ኮካ፤ ኦዳ፤ አዳሬ ጎርጣ፤ ጎዳሬ ፔንጊያ፤ ዳሪና ጉብታ፤ ጦማ ገራ ገደል፤ ላላ ዋንዳራ፤ ዳሌ ዋሻ፤ ቦራጎ ዋሻ፤ አንታሺያ ዳሞታ፤ ካዎ ሳና ዎጣሏ፤ ዎጋ አንታሺያ፤ ባውቶ እና 1,500 አመታት ዕድሜ ያለው ሶዷ ትክል ድንጋይ ወዘተ ያለበት ሲሆን ታሪካዊ ሥፍራዎች በሙሉ የየራሳቸው መነሻ ታሪክና ምክንያት ያላቸው ናቸው።
ከዳሞት ተራራ የሚነሱ ወንዞች መካከል ደግሞ "ዋላጫ ጫራቄ፤ ቦልኦ ሻፋ፤ ካዎ ሻፋ፤ ጋዜና ሻፋ፤ ዎይቦ ቁሊያ፤ ኦች ካሬ፤ ካልቴ፤ ዬቺያ ሻፋ፤ ቦርቷ ሻፋ፤ ቶቦቢ ፑልቱዋ፤ ሐማሳ ሻፋ፤ ሊንታላ ሻፋ፤ ዓዪ ካሬ ሻፋ፤ ሻጳኔ ቦታሞ" የሚባሉ በርካታ ወንዞች መፍለቂያ የሆነ ተራራ ነው።
የዳሞት ተራራና የህዝቦች ታሪክ የትናንት ሳይሆን የጥንት ወላይታዊያን አኗኗርና በርካታ የሥርዎመንግስት ታሪክ በውስጡ የያዘ ነው።
በወላይታማላ ሥርዎመንግስት ዘመን የንጉስ ሳቶ ሞቶሎሚ ሰራዊት ወይም በወላይታ ጦር ተማሪከው እዚህ ወላይታ ዳሞት የመጡ የሰሜኑ ሰዎች የዚህን ዳሞት ተራራ ትልቅነቱን ካዩ በኃላ በግዕዝ ቋንቋ "ዝባፈተን" ብሎ ይጠሩት እንደነበር የተክለሃይማኖት ገድል መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ይገኛል።
የዳሞት ተራራ ታሪክ ሲናነሳ የዳሞት መንግስት ኃያልነት አብሮ ይነሳል። በወቅቱ ሩቅ ምስራቅ ሀገራት ወይም ከአሁኗ አውሮፓ ሀገራት ጋር እንዲሁም በርካታ የምስራቁ አለም ሀገራት ለምሳሌ ማሊ፤ ቻድ፤ ኡጋንዳ፤ አዳልና ኢፋቶች ጋር የጠበቀ የኢኮኖሚ ግንኙነት የነበረው ታላቅ መንግስት የተነሳበት ሥፍራ ነው የወላይታ ዳሞት።
ዳሞት የሚለውን ስም በታች ባሉ ምስሎች ላይ የት የት እንዳሉ ማየት ይቻላል።
የዳሞት ተራራ መልማት አለበት ታሪኮቹ ለትውልድ መሻገር ይገባል ሲንል ያለምክንያት አይደለም።

5 months ago