Logo
YenetaTube
ምኩራብ፣ የቤተ መቅደሱ ባለቤት ዳግም ይመጣል

ምኩራብ ማለትም ቀጥተኛ ፍቺው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው። የዐቢይ ጾም ሶስተኛ ሣምንት በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ምኩራብ ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጥምቀቱ በፊት ወደ ቤተመቅደስ የመጣባቸው በርካታ አጋጣሚዎች ቢኖሩም፣ በተወለደ በአርባኛው ቀን የገሔደበትና በ12 ዓመቱ ከአረጋዊው ዮሴፍና ከእመቤታችን ጋር ለበዓል ወደ ኢየሩሳሌም በሄዱ ጊዜ ከእነርሱ ተለይቶ በቤተመቅደስ የኦሪት ሊቃውንትን ሲጠይቅና ሲሰማቸው የነበረበት የተለዩ ናቸው፡፡

በእነዚህ ጊዜያት አገልጋዮቹ በቤተ መቅደሱ የማይገባ ሥራ ሲሰሩ ቢያይም አምላክነቱን ገልጦ የሚያስተምርበት፣ የሚገስጽበት ጊዜ አልደረሰምና በዝምታ አልፏቸው ነበር፡፡ ከጥምቀቱ በኋላ ግን በምኩራብና በሆሳዕና ዕለታት ቤተ መቅደሱን አጽድቷል፡፡

ገዥዎችንና ለዋጮችን፣ የቤተመቅደስ አለቆችንም “ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፣ እናንተ ግን የሌቦችና የወንበዴዎች፣ የቀማኞች ዋሻ አደረጋችኋት” በማለት ገስጿል፡፡ በምኩራብ ዕለት ዮሐንስ 2÷12 እስከ ፍጻሜው ይነበባል፡፡ በቤተ መቅደሱ የሚሸጡትንም ሁሉ በጅራፍ እየገረፈ አስወጥቷል ገበታቸውንም በትኗል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም “የቤትህ ቅናት በላኝ” የሚል ቃል በመዝ. 68÷9 እንደተጻፈ አስተዋሉ፡፡

የሚሸጡት እንስሳት እንደ ብሉይ ኪዳን ሥርዓት ለኃጢአት ማስተስረያ መስዋእትነት የሚቀርቡ ነበሩ፡፡ ታዲያ የካህናት አለቆችና ግብር አበሮቻቸውም እንስሳቱ ለመስዋእት ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ መማለጃ እየተቀበሉ አገልግሎቱ መልኩን ቀይሮ ንግድ ሆኖ ነበር፡፡

እንስሳቱን የሚሸጡት ሰዎችም ስለትርፋቸው እንጂ ስለ መስዋእቱ ንጽህናና ከጌታ ስለሚገኘው ሰማያዊ ጸጋ አይጠነቀቁም ነበር፡፡ ታዲያ ወደ ቤተመቅደስ የመጣው ለፍርድ ሳይሆን ለማንፃት ነበርና ሻጮችና ለዋጮችን ሳይሆን የሚሸጡትንና የሚለወጡትን ርግቦችን፣ በጎችን፣ በሬዎችን፣ የሰዎቹን የሚለወጥ ገንዘብ ከቤተ መቅደስ አስወጣ፡፡ የቤተ መቅደሱ ባለቤት ዳግም ይመጣል፡፡ የሚመጣው ግን እንደቀደመው ለማንፃት ሳይሆን ለፍርድ ነው፡፡ ገዳማውያን ይህን ተረድተው በምግባር በሃይማኖት ጸንተው፣ በጸሎት ተግተው ይጠብቁታል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውም እንሳተፍ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-
ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-
0918077957 ወይም 0938644444

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.