Logo
FIDEL POST NEWS
የቲኩቶክ ሱስ ያስከተለው የ8.8ሚልየን ብር መርዶ፡ የአንድ አባት የዕረፍት ጊዜ ቅዠት

​በሞሮኮ ማራኬሽ የቤተሰብ ዕረፍታቸውን እያሳለፉ የነበሩት ብሪታንያዊው አንድሩ ኤ.፣ የያዙት የሥራ ስልክ እንዲህ ያለ የገንዘብ ቀውስ ይፈጥራል ብለው አልገመቱም ነበር።

ልጃቸው ለስምንት ሰዓታት ያህል በቲኩቶክ ቪዲዮዎችን በመመልከቷ ብቻ፣ ቤተሰቡ የ48,000 ዩሮ (ወደ 8.8ሚልየን ብር ገደማ) የዳታ ክፍያ ደረሰኝ ደርሶታል።

​አንድሩ እንደሚሉት፣ በውል ስምምነታቸው ላይ ከአውሮፓ ውጭ ለሚደረግ የዳታ አጠቃቀም ምንም ዓይነት የዋጋ ገደብ አለመኖሩን ባለማስተዋላቸው ለከፍተኛ ክፍያ ተዳርገዋል።

በሰዓት ከ5,700 ዩሮ በላይ ሲቆጥር የነበረው ሲስተም፣ አባቱን ለከፍተኛ ድንጋጤና ተስፋ መቁረጥ ዳርጓቸዋል።

​ይህ አጋጣሚ የአውሮፓ ኮሚሽን በቲኩቶክ ላይ "ሰዎችን ለሱስ የሚያጋልጡ አሰራሮች አሉት" በሚል ምርመራ እያጠናከረ ባለበት ወቅት የተከሰተ ሲሆን፣ የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ በታዳጊዎች አዕምሮ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳትም በድጋሚ አነጋጋሪ አድርጎታል።

Daily Mail
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.