Logo
FIDEL POST NEWS
በሱዳን የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን የተመድ ሪፖርት አመለከተ

​በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ግጭት የሚያጠናው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ገለልተኛ መርማሪ ቡድን ዛሬ ሐሙስ ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል ዳርፉር ክልል "የዘር ማጥፋት" (Genocide) መፈጸሙን የሚያሳዩ ግልጽ ምልክቶች መገኘታቸውን አስታወቀ።


​የአል-ፋሽር እልቂት፦ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል (RSF) የተባለው አማጺ ቡድን ያለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የአል-ፋሽር ከተማን ሲቆጣጠር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውና መደፈራቸው ተገልጿል።

​የዘር ጥቃት፦ ጥቃቱ በተለይም አረብ ባልሆኑ ማህበረሰቦች (በተለይ ዛጋዋ እና ፉር ጎሳዎች) ላይ ያነጣጠረና ጎሳን መለየት መሠረት ያደረገ እንደነበር ተረጋግጧል።

​የ18 ወራት ከበባ፦ ከተማዋ ከመያዟ በፊት ለ18 ወራት የተደረገው ከበባ፣ ማህበረሰቡን በረሃብና በስቃይ ለማጥፋት ታስቦ የተደረገ የዘር ማጥፋት ተግባር ነው ተብሏል።

​ዓለም አቀፍ ምላሽ፦ የመርማሪ ቡድኑ ሰብሳቢ መሐመድ ቻንዴ ኦስማን እንደገለጹት፣ ወንጀሉ በድንገት የተፈጸመ ሳይሆን በከፍተኛ የRSF አመራሮች የታቀደና የተቀናጀ የዘር ማጥፋት ተግባር ነው።

​⚠️ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች፦
ሪፖርቱ በከተማዋ ውስጥ አስከፊ የሆኑ የጅምላ ግድያዎች፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየትና ሰዎችን የማፈን ድርጊቶች በስፋት መፈጸማቸውን በዝርዝር አስፍሯል።
​የሱዳን መንግስትም ሆነ RSF እስካሁን ለቀረበባቸው ወቀሳ ይፋዊ ምላሽ አልሰጡም።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.