Logo
YenetaTube
"ዘረኛ አይደለሁም፤ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው" — ጂያንሉካ ፕሪስቲያኒ

አዲስ አበባ — ትናንት ምሽት በተደረገው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ላይ በሪያል ማድሪዱ ኮከብ ቪኒሺየስ ጁኒየር የቀረበበትን የዘረኝነት ክስ አስመልክቶ አርጀንቲናዊው ተሰጥኦ ጂያንሉካ ፕሪስቲያኒ (Gianluca Prestianni) አስቸኳይ ምላሽ ሰጥቷል።

በጨዋታው ወቅት በሁለቱ ተጫዋቾች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ቪኒሺየስ ጁኒየር "ዘረኛ ስድብ ተሰድቤያለሁ" የሚል ክስ ማቅረቡን ተከትሎ ወጣቱ የቤንፊካ ተጫዋች ፕሪስቲያኒ በሰጠው መግለጫ ድርጊቱን በጽኑ አስተባብሏል።

ፕሪስቲያኒ በመግለጫው ለሪያል ማድሪዱ ተጫዋች ቪኒሺየስ ጁኒየር በማንኛውም ሰዓት የዘረኝነት ስድብ አለመሰንዘሬን ላረጋግጥ እወዳለሁ" ብሏል።

ቪኒሺየስ ከእኔ ሰማሁት ብሎ ያሰበው ነገር "በሚያሳዝን ሁኔታ የተሳሳተ ግንዛቤ" (Misunderstanding) መሆኑን ገልጿል።

ተጫዋቹ አክሎም "በህይወቴ በማንም ላይ ዘረኛ ሆኜ አላውቅም" ካለ በኋላ ከሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች በኩል ደረሰኝ ስላለኝ ዛቻ ማዘኑን ገልጿል።

ይህ ክስተት በሻምፒዮንስ ሊጉ መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተ ሲሆን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) በጉዳዩ ላይ ምርመራ ሊጀምር እንደሚችል ይጠበቃል።

የኔታ ሚዲያ

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.