Logo
YenetaTube
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የነዳጅ ምርት መፈተሻ ላብራቶሪ በድሬዳዋ ልትከፍት ነው

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የነዳጅ ምርት መፈተሻ ላብራቶሪ በድሬዳዋ ከተማ በቅርቡ ልትከፍት መሆኑን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ላብራቶሪው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የነዳጅ ምርቶችና ዘይቶች የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ማሟላታቸውን ለመፈተሽ የሚያስችል ነው።

አገልግሎቱ በቅርበት መሰጠቱ አምራች ድርጅቶችና ተቋማት በተቀላጠፈ መንገድ ጥራት ማረጋገጥ እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለዚህም ዘመናዊ መሣሪያዎችና የሰለጠኑ ባለሙያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

ተቋሙ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳና በባሕር ዳር ተጨማሪ የፍተሻ ላብራቶሪዎችን በማደራጀት ላይ እንደሚገኝም ነው ያስገነዘቡት።

@ጋዜጣ_ፕላስ

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.