Logo
FastMereja
ጨረቃ ማክሰኞ ምሽት ከታየች የ1447ዓ.ሒ የታላቁ ረመዷን ፆም ረቡዕ ካልታየች ግን ሐሙስ እንደሚሆን ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ገለፀ።

የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በላከው መግለጫ ጨረቃ ማክሰኞ የካቲት 10/18 (ሻዕባን 29/1447) ከታየች የ1447 ዓ.ሒ የታላቁ ረመዷን ፆም ረቡዕ የካቲት 11/18 ዓ.ል የሚጀመር ሲሆን ካልታየች ግን ሐሙስ የካቲት 12/18 ዓ.ል እንደሚጀምር ገልጿል።

ለተከበረው የረመዷን ወር ፆም በሰላም ላደረሰን አሏህ ምስጋና እናቀርባለን ያለው የፌዴራሉ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ህዝበ ሙስሊሙ በፆም ወቅት ኢስላማዊውን የመደጋገፍና የመረዳዳት ተግባር የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አደራ ብሏል።

ረመዷን የጤና፣ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንም ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ መልካም ምኞቱን ለመላው ህዝበ ሙስሊም ገልጿል።

የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.