Logo
FastMereja
ዛሬ አንድ የሙዚቃ አቀናባሪ ወዳጄጋ ስንጨዋወት እንዴት ነው የሰሞኑ የነ ልጅ ሚካኤል እሰጣ ገባ ብለው ፈገግ ብሎ ባጭሩ ልንገርህ ብሎ እንዲህ አለኝ

ልጅ ማይክን ከአንድም ሁለት ጊዜ አግኝቸዋለሁ በዚ የራፕ ሙዚቃ ዘርፍ ላይ በጣም እስማርት እና ቢዝነሱ የገባው ልጅ ነው የሱን ሙዚቃ የሚሰማውንም የማይሰማውንም እንዲሰማ ያደርጋል አሁን ይሄን ግርግር ያስነሳው ሆን ብሎ ነው ብዬ አስባለሁ ምክንያቱም ልብ ብለህ ከሆነ ማንም ምንም ሳይለው ብቻ በድንገት በፊት ራፕ የምትሰሩ ልጆች ብንከባበር ይሻላችዋል ብሎ በፅሁፍ መልክት አስተለለፈ በቃ ባጭሩ ስነግርህ ይቺ በፊት አብረውት ይሰሩ የነበሩ ግን ደሞ የጠፉ ጏደኞቹን ስቦ የማስገቢያ ሲስተም ነች ከዛ በፍጥነት ዜማ የሚል ሙዚቃና ቪዲዮ ለቀቀ ተዘጋጅቶበት እንደነበር በደንብ ያስታውቃል::

አሁን እንደምታየው የበፊት ራፐሮች ጠቅላላ በተቃራኒ ጎን የቆሙ በመምሰል ሁሉም እየገቡ ማህበራዊ ሚዲያውን ያዙት አሁን ትንሽ ቆይተው ሁሉም አልበም እንለቃለን ሲሉ ትሰማለህ ትልቅ ፕሮሞሽን ነው የሰራላቸው ካወቁበት መጠቀም ከቻሉ ይሄ ጊዜ ይጠቅማቸዋል እራሳቸውንም ያወጡበታል እንጂ ልጅ ሚካኤል ምን ፍለጋ እዚ ውስጥ ይገባል ብለህ ታስባለህ አሁን እሱ ድልድይ ሆኗቸዋል ከአሁን በዋላ የነሱ ጉዳይና ጉብዝና ነው የሚወስነው በእርግጠኝነት ግን የምነግርህ እሱን እዚ ግርግር ውስጥ ድጋሚ አናየውም ብሎ ሚስጥራቸውን ጀባ አለኝ እላችዋለሁ

እንኳንም ፆም ደረሰ እራፐር ይፁም አይፁም አላቅም እኛ ግን እንፁምበት ተውን በሏቸው::
Via: ደረጄ ብርሀን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.