Logo
FIDEL POST NEWS
​💍 የፍቺን ቁጥር ለመቀነስ አዲስ ስልት፡ በኢትዮጵያ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና የግዴታ ሊሆን ነው

​ከጊዜ ወደ ጊዜ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ አስገዳጅ አሰራር ይፋ አደረገ።

​የግዴታ ስልጠና፦ ማንኛውም ሰው ወደ ጋብቻ ከመግባቱ በፊት የቅድመ ጋብቻ ስልጠና ወስዶ ሰርተፊኬት መያዝ ይኖርበታል።

​መቼ ይጀመራል?፦ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአረጋውያንና ቤተሰብ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ሮበሌ እንደገለጹት፣ አሰራሩ በ2019 ዓ.ም በይፋ ስራ ላይ ይውላል።

​ትብብር፦ ስራው ከሃይማኖት ተቋማት እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ታውቋል።

​📉 የፍቺው መጠን መጨመር
የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጄንሲ በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት፣ የፍቺ መጠን ካለፉት ዓመታት አንፃር የ 54 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህ አሃዝ የቤተሰብ መፍረስ ለሀገር ደህንነት ስጋት እየሆነ መምጣቱን ያሳያል።

​💡 መፍትሔው ምንድነው?
ሚኒስቴሩ ለትዳር መፍረስ ዋነኛው ምክንያት "ስለ ትዳር ያለው የግንዛቤ እጥረት" መሆኑን በመለየት የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦

​የስልጠና ማኗሎች፦ ጥምር ጥናትን መሰረት ያደረጉ የማስተማሪያ ሰነዶች ተዘጋጅተዋል።

​የጋራ ፎረም፦ በቤተሰብ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ተቋማት በጋራ የሚመክሩበት ፎረም ተመስርቷል።

​"ለሀገር ለውጥ ከቤተሰብ መጀመር አለብን፤ በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊየን በላይ ቤተሰቦች አሉ" — አቶ ተስፋዬ ሮበሌ

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ ምስል
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.