በአመት ከ44,000 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ከአፈጣጠር ችግር ጋር ይወለዳሉ!
#fastmereja I እሊያንስ ፎር በርዝ ድፌክት (አብዲ) ከሪች እናዘር ፋውንዴሽንና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር በነርቭ ዘንግ ክፍተት እና ሀይድሮሴፋለስ(Spina Bifida and Hydrocephalus) በሽታ ዙሪያ ላይ ያተኮረ የጋዜጠኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬዉ እለት በሞናርክ ሆቴል ተካሂዷል።
ስፓይና ቢፊዳ (የነርቨ ዘንግ አፈጣጠር ) ችግሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የአከርካሪ አጥንትና የህብለ ሰረሰር በአግባቡ አለመዘጋት/ክፍተት ነው፡፡
ሃይድሮሴፋለስ (የጭንቅላት ውስጥ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት) ሲሆን ይህም የአዕምሮ ግፊት እንዲጨምርና የራስ ቅል ላይ መሰንጠቅን ሊያስከትል ይችላል።
ስልጠናዉ የነርቭ ዘንግ ክፍተትን ለመከላከል እና ስለችግሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለዉን ግንዛቤ ለማሳደግ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም እነዚህ ህፃናት በዚሁ ህመም ምክንያት ለእድሜ ልክ የመንቀሳቀስ ችግር እና እራሳቸውን ችለው የመፀዳዳት ችግር እንደሚገጥማቸዉ ነዉ የተገለፀዉ፡፡
ፎሊክ አሲድ እጥረትን ለመከላከል እናቶች በመጀመሪያ የእርግዝና ወራቶች በእንክብል መልክ የሚሰጥ መድሃኒት መውሰድ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ስንዴ፣ ዘይት፣ ጨው የበለፀጉ ምግቦችን መውሰድ የፎሊክአሲድ ችግርን ለመቅረፍ ወሳኝ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም በችግሩ የተጎዱ ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው ጥራቱን የጠበቀ ህክምና እንዲሁም የእለት ተእለት ህይወታቸዉን በአግባቡ እንዲመሩ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባ ነዉ የተገለፀዉ።

6 months ago