Logo
Getu Temesgen
"በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም" - ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በዛሬ የፓርላማ ማብራሪያቸው አሜሪካ ስለህዳሴ ግድቡ በተደጋጋሚ ለምትለፍፈው ጉዳይ እክት ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ "ለህዳሴ ግድቡን በገንዘብ ረድታለች" በማለት ከሦስት ጊዜ በላይ መናገራቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ በዋይትሃውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም፣ "ዩናይትድ ስቴትስ የህዳሴ ግድብን በገንዘብ በማገዟ ኃላፊነት ትወስዳለች" ሲሉ ተደምጠው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ደግሞ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፣ "በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም" ሲሉ አክት ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።

"በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ ጠቋም በሀገር ውስም በከሀገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነት ጨከሰነው በጋራ ቆመው ስለሰሩ የተከወነ ፕሮጀክት ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

አቢይ (ዶ/ር) ይህን ያሉት ሜጋ ፕሮጀክቶች እምብዛም ስለሌሉ ወጣቶች ለስራ አጥነት ጨምር እየተጋለጡ በመሆኑ ምላሽ እንዳጠሱ ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ ሲሆን፣ ከዚህ ንግግራቸው አስከትለውም፣ "ግን በዚህ አላበቃም፤ ህዳሴ ከአፍሪካ አንደኛውን ሰርተናልና ሌላ አያስፈልግም እኮ አላለችም ኢትዮጵያ" ብለዋል።

"በአፍሪካ ሦስተኛውንም ኮይሻ እየገነባን ነው ያለነው። የንፋሱን ሳንጨምር። በርካታ ፕሮጀክቶች ይሰራሉ" ነው ያሉት።

"'ፕሮጀክቶ ቋሟል፤ ሜጋ፣ ሜጋ ፕሮጀክት የለም' ለተባለው። እውነት ነው ፕሮጀክት የለም። ግን ከአፍሪካ አንደኛው ኤርፓርት ኢትዮጵያ ውስጥ ተጀምሯል" ሲሉ መልሰዋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #thiqah #pm #abiy

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.