የዳላይ ላማ የመጀመሪያው የግራሚ ሽልማት እና የቤጂንግ ተቃውሞ
የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ በ90 ዓመታቸው የመጀመሪያውን የግራሚ ሽልማት ማግኘታቸውን ተከትሎ ቻይና ጠንካራ ተቃውሞ አሰማች።
ሽልማቱ፦ ዳላይ ላማ በ68ኛው የግራሚ ሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ "Meditations: Reflections on His Holiness the Dalai Lama" በተሰኘው የድምፅ መጽሐፍ (Audiobook) "ምርጥ ትረካ እና ታሪክ አቀራረብ" በሚል ዘርፍ አሸንፈዋል።
የዳላይ ላማ ምላሽ፦ "ይህ ሽልማት የግል ስኬቴ ሳይሆን የሰው ልጅ የጋራ ሃላፊነት እውቅና ነው" በማለት በምስጋና ተቀብለውታል።
የቻይና ተቃውሞ፦ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያንግ፥ "ሽልማቱ በቻይና ላይ ለሚደረግ የፖለቲካ መጠቀሚያነት የዋለ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
ቤጂንግ ምን አለች?፦ ዳላይ ላማ "በሃይማኖት ስም የተሸፈኑ ተገንጣይ" ናቸው ስትል የከሰሰችው ቻይና፣ ሽልማቱ ጸረ-ቻይና ለሆኑ እንቅስቃሴዎች እንደ መሳሪያ ማገልገሉን እንደማትቀበል ገልጻለች።
ዳላይ ላማ እ.ኤ.አ. ከ1959 ጀምሮ በህንድ በስደት የሚገኙ ሲሆን፣ ቻይና ቲቤትን እንደ ግዛቷ ስለምትቆጥር የእሳቸውን ማንኛውንም ዓለም አቀፍ እውቅና በጽኑ ትቃወማለች።

6 months ago