Logo
FIDEL POST NEWS
የአሜሪካ የበረዶ ማዕበል

​በአሜሪካ ከፍተኛ የበረዶ ማዕበል (Winter Storm Fern) በመከሰቱ የሰዎች ህይወት እየጠፋ ሲሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደግሞ ያለ መብራት ተቸግረዋል።

​የሟቾች ቁጥር፦ እስካሁን በደረሰው መረጃ መሰረት ቢያንስ 15 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ኒው ዮርክ ሲቲ ውስጥ 5 ሰዎች በብርድ ምክንያት ሞተው ተገኝተዋል።

​የመብራት መቆራረጥ፦ በመላ ሀገሪቱ ከ 800,000 በላይ ቤተሰቦች ያለ መብራት ይገኛሉ። በተለይ ቴነሲ (Tennessee)፣ ሚሲሲፒ እና ሉዊዚያና በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል።

​የበረራ መቋረጥ፦ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስካሁን ከ 14,000 በላይ በረራዎች ተሰርዘዋል። ይህም በአሜሪካ አቪዬሽን ታሪክ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

​የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፦ ኒው ዮርክን ጨምሮ ከ 20 በላይ ክፍለ ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።

​የባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ፦
የኒው ዮርክ ሲቲ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ እና የክፍለ ግዛቷ ገዢ ካቲ ሆኩል ህዝቡ ከቤቱ እንዳይወጣ አጥብቀው አሳስበዋል።

ሙቀት እስከ -49 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊወርድ እንደሚችልና ሁኔታው ገና "መጀመሪያው ላይ" እንደሆነ ተገልጿል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.