ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ከ2026-2030 ያለውን ብሔራዊ ፍኖተ-ካርታ ይፋ አደረጉ
ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በትናንትናው እለት ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ-መጠይቅ ኤርትራ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የምትከተለውን ስትራቴጂካዊ የልማት ዕቅድ ያብራሩ ሲሆን በሌላ በኩል በአፍሪካ ቀንድ እየታየ ባለው ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ዙሪያ ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው መጀመሪያ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራው አንድ ዋልታ (Unipolar) የዓለም ሥርዓት እያበቃለት መሆኑን ገልጸዋል።
ዋሽንግተን ያለባት የ36 ትሪሊየን ዶላር ዕዳ እና በዚያ አገር ውስጥ ያለው የፖለቲካ ክፍፍል የምዕራባውያን የበላይነት ማብቂያ ምልክቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የአፍሪካ አገራት ይህንን የሽግግር ወቅት በመጠቀም ሉዓላዊ ተቋማትን መገንባት እንዳለባቸውና "ዘመናዊ ባርነት" ካሉት የውጭ እርዳታ ጥገኝነት መውጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ከአዲስ አበባ ጋር እየተባባሰ የመጣውን ግንኙነት አስመልክቶ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በቅርቡ የሚሰማው "የባሕር በር ሉዓላዊ ባለቤትነት" ንግግር በውጭ ኃይሎች የሚገፋ "ጂኦ-ፖለቲካዊ ሴራ" ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ትንኮሳ አዘል ንግግሮችን ትቶ ትኩረቱን በገዛ አገሩ ውስጥ ባሉ ውስጣዊ ቀውሶች ላይ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
ኤርትራ "የጦርነት ፍላጎት የላትም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ነገር ግን ጥቃት ከተሰነዘረባት ሉዓላዊነቷን ለመከላከል ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
በአገር ውስጥ ልማት ረገድ ፕሬዝዳንቱ በኢነርጂ፣ በምግብ ዋስትና እና በሰው ኃይል ልማት ላይ ያተኮረ ትልቅ ዕቅድ ይፋ አድርገዋል
በመጀመሪያው ምዕራፍ 12 አነስተኛ የኤሌክትሪክ ፍርግርጎችን በመጠቀም 360 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት የታቀደ ሲሆን በቀጣይ ከፀሐይ ከነፋስ እና ከጂኦ-ተርማል 2000 ሜጋ ዋት ለማድረስ ታቅዷል።
ለወደፊቱ የኒውክሌር ኃይል ማመንጨትም እንደታሰበ ጠቁመዋል።
የትምህርት ሥርዓት ለውጥ ከኪንደርጋርተን እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ያለውን ሥርዓት በአዲስ መልክ መቃኘት የአገሪቱ ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
የኤርትራ ዲያስፖራ በማዕድን በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች በቀላሉ መሳተፍ እንዲችል ዲጂታል የመረጃ ቋት (Database) እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል።
የሱዳንን ቀውስ በተመለከተ ኤርትራ የዜግነት መብትን መሠረት ያደረገ ሽግግር እንዲኖር የምታደርገውን ጥረት እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
ቀጣናዊ ትስስር አስፈላጊ ቢሆንም ይህ መሠረት ሊኖረው የሚገባው በቅን ልቦና እንጂ በተንኮል መሆን የለበትም ብለዋል።
ዋናው አጀንዳችን የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ነው.. የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደማይረባ ጦርነት ውስጥ አታስገቡት ትኩረታችሁን እውነተኛ ችግሮቻችሁን በመፍታት ላይ አድርጉ ብለዋል ::
ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የብልፅግና ፓርቲን ስም በቀጥታ ባይጠቅሱም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራውን አስተዳደር እና የፓርቲውን ፖሊሲዎች በሚመለከት የሰነዘሯቸው ጠንከር ያሉ ነጥቦች አሉ።
በንግግራቸው ውስጥ ስለ ገዥው ፓርቲ እና ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው
ፕሬዝዳንቱ የብልፅግና መንግሥት የሚያነሳውን የባሕር በር ጥያቄ ከእውነታ የራቀ ቅዥት እና ትኩረት ማዘናጊያ ነው በማለት ነቅፈዋል።
ፓርቲው በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን መዋቅራዊ እና የኢኮኖሚ ውድቀቶች ለመሸፈን ሲል የውጭ ጠላት ወይም አዲስ አጀንዳ የመፍጠር ዝንባሌ እያሳየ ነው የሚል ትችት ሰንዝረዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የብልፅግና ፓርቲ አመራር የኢትዮጵያን ውስጣዊ ቀውሶች (በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ግጭቶችን) መፍታት ተስኖታል ብለዋል።
የራሱን ቤት ማፅዳት ያልቻለ አካል የጎረቤቱን ቤት በር ያንኳኳል በሚል ዘይቤ ፓርቲው የውስጥ ፖለቲካ ትኩሳቱን ወደ ቀጣናዊ ግጭት ለመቀየር እየሞከረ ነው ሲሉ ከስሰዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የብልፅግና መንግሥት በውጭ ኃይሎች (በተለይም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን እና የምዕራባውያን ኃይሎችን በመጥቀስ) ፍላጎት እየተመራ ነው የሚል እምነት አላቸው።
የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካ በመከተል አገሪቱን ለባዕዳን ጂኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎት አሳልፎ እየሰጠ ነው የሚል ወቀሳ አቅርበዋል።
በ2018 (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር) የተፈረመው የሰላም ስምምነት በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ሊሆን ያልቻለው በብልፅግና ፓርቲ "ስትራቴጂካዊ ስህተት" እና "የቃል ኪዳን ማጠፍ" ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።
ፓርቲው አጋርነትን ሳይሆን የበላይነትን ይፈልጋል የሚል አንድምታ ያለው ንግግር አድርገዋል።
ምንም እንኳን የብልፅግና ፓርቲ "መደመር" እና "ብሔራዊ አንድነት" በሚሉ መፈክሮች ቢነሳም ፕሬዝዳንቱ ግን ፓርቲው አሁንም በዘር ላይ የተመሰረተውን ክፍፍል ማስቀጠልን እንደ ስልጣን ማቆያ እየተጠቀመበት ነው ሲሉ ተችተዋል።
ይህ አካሄድ ደግሞ ኢትዮጵያን ወደ መበታተን እንደሚወስዳት አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸው አመለካከት ከ"ስልታዊ አጋርነት" ወደ "ጥልቅ ጥርጣሬ እና ፍጥጫ" መሸጋገሩን ንግግራቸው በግልጽ ያሳያል።

7 months ago