ዛሬ ምሽት በሀዋሳ ከተማ "አጠና ተራ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከባድ የእሳት አደጋ ተከሰተ
በሀዋሳ ከተማ ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መስመር "አጠና ተራ" ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በአሁኑ ሰዓት ከባድ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተሰምቷል።
ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች;
📍 አካባቢው፦ እሳቱ የተነሳው ከአጠና ተራ አቅራቢያ ሲሆን፣ በአቅራቢያው ትልቅ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር መኖሩ አደጋው ወደ የከፋ ደረጃ ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
🕑 የቆይታ ጊዜ፦ እሳቱ ከተነሳ ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ ጭሱ ከወልደ አማኑኤል አደባባይ ወደ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ ላይ በግልጽ እየታየ ይገኛል።
🚒 የመከላከል ጥረት፦ አንድ የእሳት አደጋ መኪና ወደ ስፍራው ደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ የያዘው ውሃ አልቆበት በመመለሱ አደጋውን በአፋጣኝ መቆጣጠር አልተቻለም።
🤝 የህዝቡ ርብርብ፦ በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ነዋሪዎች የሚችሉትን ሁሉ በመጠቀም እሳቱን ለማጥፋት በከፍተኛ ርብርብ ላይ ይገኛሉ።
⚠️ አስቸኳይ ጥሪ፦ የሚመለከተው አካልና ተጨማሪ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪናዎች በአፋጣኝ ደርሰው አደጋው ሳይባባስና በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሳያደርስ እንዲቆጣጠሩ ነዋሪዎች ጥሪያቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስተላልፈዋል።

7 months ago