Logo
Getu Temesgen
🏠 ራይድ ቃል ገባ... ቃሉንም ፈፀመ!

"ራይድ ለታማኝ ደንበኛው የመኖሪያ ቤት አበረከተ"
#ethiopia | ​ሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ ትራንስፖርት) በቅርቡ ባስጀመረው የሎተሪ መርሃ ግብር አሸናፊ ለሆኑት ወ/ሮ ሕይወት ደበላ የመኖሪያ ቤት ሽልማትን አስረክቧል።

​ወ/ሮ ሕይወት ላለፉት 3 እና 4 ዓመታት የራይድ ደንበኛ ሲሆኑ፤ ዛሬ የቤት ባለቤት ሆነው የቤቱን ቁልፍ ተረክበዋል።

​"የሰውን ህይወት መቀየር እናምናለን!"

የራይድ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤

​"ራይድ ማንኛውንም ዓይነት ኢኒሼቲቭ ይዞ ሲመጣ የሰውን ሕይወት መቀየር አለበት ብለን እናምናለን። ዓላማችን የአሸናፊዎችን የቤት ኪራይ እና መሰል ወጪዎችን በማቃለል የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ማስቻል ነው።"

​ቀጣዩ እድለኛ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ!

ድርጅቱ ይህ የሽልማት መርሃ ግብር በዚህ እንደማያበቃ እና ወደፊትም በተሻሉ ሽልማቶች እንደሚቀጥል አብስሯል። በቀጣይ የሚኖሩትን አበረታች ዝግጅቶች በቅርቡ ይፋ ይደረጋሉ።

​እንኳን ደስ አለዎት! 👏

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

​#ride #hybriddesigns #housewinner #samrawitfikru #lifechanging #addisababa #ethiopia

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.