7 months ago
የራይድ ትራንስፖርት እና የቦስተን ፓርትነርስ (ኩሪፍቱ) ታሪካዊ የሥራ ስምምነት ተፈራረሙ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፖርት ፈር ቀዳጅ የሆነው ራይድ ትራንስፖርት፣ በቱሪዝምና መስተንግዶ ዘርፍ ግዙፍ ስም ካለው ቦስተን ፓርትነርስ ጋር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በጋራ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተፈራርሟል።
የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት፦
ራይድ የኤሌክትሪክ መኪኖቹን እንደ እንጦጦ ፓርክ፣ አፍሪካ ቪሌጅ እና ኩሪፍቱ ቢሾፍቱ ባሉ የቱሪስት መስህቦች በመመደብ ከቦስተን ፓርትነርስ ጋር በጋራ ይሰራል።
ለታላላቅ ሁነቶች አስተማማኝ ትራንስፖርት፦
በኩሪፍቱ ሪዞርቶች በሚካሄዱ ትልልቅ ስብሰባዎች፣ የጋብቻ ሥነ ሥርዓቶችና ኮንሰርቶች ወቅት ራይድ በቂና አስተማማኝ ትራንስፖርት ያቀርባል።
ዘመናዊ የቱሪስት ትራንስፖርት፦
ለኩሪፍቱ ሪዞርትና ለቦስተን ስፓ ደንበኞች ያለምንም እንግልት የሚንቀሳቀሱበት ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ይቀርባል።
የጋራ የገበያ ትስስርና ፕሮሞሽን፦
ሁለቱ ተቋማት የጋራ የገበያ ትስስር፣ የማስተዋወቅና የብራንድ ግንባታ ሥራዎችን በትብብር ያከናውናሉ።
አዳዲስ ፓኬጆች፦
የገበያ ተደራሽነትን የሚያሰፉ አዳዲስ የጋራ ፓኬጆችን በማዘጋጀት ለተጠቃሚዎች ያቀርባሉ።
የራይድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሳምራዊት ፍቅሩ ስምምነቱ ሰዎችን ከዕድሎች ጋር የማገናኘት ራዕያቸውን ይበልጥ እንደሚያሳልጠው ገልጸዋል።
የቦስተን ፓርትነርስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታዲዎስ ጌታቸው በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው ላለፉት 24 ዓመታት የጀመረውን አዳዲስ የቱሪዝም አገልግሎቶችን የማቅረብ ጉዞ ይህ ስምምነት ይበልጥ እንደሚያዘምነው ተናግረዋል።
#getu #ethiopia #ride #bostonpartners #kuriftu #tourism #digitaltransport #businessnews #samrawitfikru #tadiwosgetachew #ራይድ #ኩሪፍቱ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

9 months ago
🏠 ራይድ ቃል ገባ... ቃሉንም ፈፀመ!
"ራይድ ለታማኝ ደንበኛው የመኖሪያ ቤት አበረከተ"
#ethiopia | ሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ ትራንስፖርት) በቅርቡ ባስጀመረው የሎተሪ መርሃ ግብር አሸናፊ ለሆኑት ወ/ሮ ሕይወት ደበላ የመኖሪያ ቤት ሽልማትን አስረክቧል።
ወ/ሮ ሕይወት ላለፉት 3 እና 4 ዓመታት የራይድ ደንበኛ ሲሆኑ፤ ዛሬ የቤት ባለቤት ሆነው የቤቱን ቁልፍ ተረክበዋል።
"የሰውን ህይወት መቀየር እናምናለን!"
የራይድ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤
"ራይድ ማንኛውንም ዓይነት ኢኒሼቲቭ ይዞ ሲመጣ የሰውን ሕይወት መቀየር አለበት ብለን እናምናለን። ዓላማችን የአሸናፊዎችን የቤት ኪራይ እና መሰል ወጪዎችን በማቃለል የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ማስቻል ነው።"
ቀጣዩ እድለኛ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ!
ድርጅቱ ይህ የሽልማት መርሃ ግብር በዚህ እንደማያበቃ እና ወደፊትም በተሻሉ ሽልማቶች እንደሚቀጥል አብስሯል። በቀጣይ የሚኖሩትን አበረታች ዝግጅቶች በቅርቡ ይፋ ይደረጋሉ።
እንኳን ደስ አለዎት! 👏
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ride #hybriddesigns #housewinner #samrawitfikru #lifechanging #addisababa #ethiopia

Comments