" ዛሬ ኤፍኤም ባስ አሊዶሮ ታግቶ መኪናውም በጥይት ተመትቷል፤ ብዙ መኪና ቆሞ ነበር " - መንገደኛ
➡️ " የደረሰን መረጃ ሾፌሮችና በአውቶብሱ የተሳፈሩ ሰዎች ታግተዋል የሚል ነው " - ማህበሩ
በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል ገብረ ጉራቻ ፊቸ መካከል በሚገኘው መንገድ "አሊደሮ" ተብሎ በሚጠራው ልዩ ቦታ በአገር አቋራጭ ተሽከርካሪ ሲጓዙ የነበሩ በርካታ ተሳፋሪዎችና ሾፌሮች በታጣቁ አካላት መታገታቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር እና የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
ተሳፋሪዎቹ መነሻቸውን አዲስ አበባ በማድረግ ወደ ደብረ ማርቆስ ሲጓዙ እንደነበር በመግለጽ አንዳንዶች የታጋቾችን ቁጥር " 40 " ያደረሱት ሲሆን፣ የተመቱም ሳይኖሩ እንዳልቀረ ደግሞ ከቦታው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የዓይን እማኝ መንገደኛ፣ " ዛሬ ኤፍኤም ባስ አሊዶሮ ታግቶ መኪናውም በጥይት ተመትቷል፤ ብዙ መኪና ቆሞ ነበር " ሲሉ ከቦታው የተመለከቱትን ገልጸዋል።
እንዲሁም፣ "ኤፍኤም ባስ" የሚል ስያሜ ያለው የህዝብ መጓጓዣ ተሽከርካሪ፣ የጎን መስታውቱ ተገንጥሎ፣ በጋቢናው በኩል በጥይት ተበሳስቶ የሚያሳይ ቪዲዮ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራው ደርሶታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለእገታው ዝርዝር ማብራሪያ የጠየቀው የኢትዮጵያ አባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር፣ " የደረሰን መረጃ ሾፌሮችና በአውቶብሱ የተሳፈሩ ሰዎች ታግተዋል የሚል ነው " ብሏል።
እገታ የተፈጸመበት ልዩ ቦታ "አሊዶሮ" መሆኑን የገለጹት አንድ የማህበሩ አመራር፣ " ቦታዋ በጣም መጥፎ ነች። ይሄን አንድ ወር ግን ጥሩ ነበር፤ ተሽከርካሪዎች በእጀባ ነበር የሚሄዱት። ሾፌሮቹ የሆነ ቦታ ተጠራቅመው በርከት ሲሉ በወታደር ታጅበው ያልፉ ነበር " ሲሉ አስረድተው፣ የዛሬው ጥቃት የደረሰባቸው ግን ያን ጥሰው ይሁን ያለአጃቢ ሄደው ገና እንዳልታወቀ ገልጸዋል።
ማህበሩ፣ " ከፍቼ ጎሀፂዮን መስመር የህዝብ አውቶብድ ተሳፋሪዎች በዘራፊዎች መታገታቸውን መረጃዎች ደርሰውናል " ሲል አስታውቆ፣ " አሁን የምንሰማው ነገር ግን የሚያሳዝን ነው " ሲልም መረጃ አጋርቷል።
የሾፌሮችን ውሎ በየእለቱ የሚከታተለው፣ " የሾፌሮች አንደበት "፣ " ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ ፊቸ መሀል ባለው የመንገድ ክፍል አሊደሮ ላይ የህዝብ አውቶብስ ተሳፋሪ የተወሰኑና ሌሎች ሾፌሮች በዘራፊ ወንበዴዎች ታፍነው ተወስደዋል የሚል መልዕክት ደርሶናል " የሚል መረጃ አጋርቷል።
የታጠቁ አካላት " ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ በመክፈት፣ ተሳፋሪን በመምታት የተወሰኑትን በማፈን፣ ሌሎች የከባድ መኪና ሾፌሮችንም በማገት ይዘው መሄዳቸውን መልዕክት ደርሶናል " ነው ያለው።
" በአቅራቢያው የነበረ ህግ አስከባሪዎች በቦታው ደርሰው የተኩስ ልውውጥ ቢያደርጉም ሌላው ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርሱ ከመከላከል ውጭ የታገቱትን ማስጣል እንዳልተቻለ " የሚገልጽ መረጃ እንደደረሰውን አሳውቋል።
" በዚህ የመንገድ ክፍል ያለ ጉዞ በእጀባ ቢሆንም አልፎ አልፎ በመሀል እየገቡ የሚያፍኑበት ሂደት ትልቅ ስጋት እና ጉዳትን እያላበሰ ይገኛል " ሲል የሁነቱን አስከፊነት አስረድቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#tikvahethiopiafamilyaa
tikvahethiopia

7 months ago