Logo
FIDEL POST NEWS
በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ሳምንታት በማርበርግ ቫይረስ በሽታ የተያዘ ወይም ምልክቶችን ያሳየ ሰው አለመገኘቱን ጤና ሚኒስቴር ገለፀ

ሚኒስቴሩ በአሁኑ ወቅት ከተረጋገጠ የማርበርግ ታማሚ ጋር ንክኪ ኖሮት ክትትል የሚደረግለት ሰው የለም ያለ ሲሆን አሁንም ግን በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሳይዘናጉ እና ችላ ሳይሉ የማሕበረሰብ አቀፍ የበሽታ መከላከያ መንገዶችን እና የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ተግባቦቶችን ለሚቀጥሉት ተጨማሪ 21 ቀናት በይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥሉ ጠይቋል ።

ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ታማሚ ከተገኘበት ሕዳር 5 ቀን 2018 ዓ/ም
ጀምሮ እስከ ዛሬ ታሀሳስ 27/2018 ዓ/ም ድረስ በአጠቃላይ በበሽታው ለተጠረጠሩ 3800 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 14ቱ የማርበርግ ቫይረስ እንደተገኘባቸውም ገልፆ ከእነዚህም ውስጥ ዘጠኙ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አምስቱ ደግሞ ከበሽታው ማገገም ችለዋል ብሏል።

ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሆኖ ባደረገው ርብርብና ያለሰለሰ ጥረት ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ መቆጣጠር የተቻለ መሆኑን ሚኒስቴሩ ጠቅሶ በዚህ ወረርሽኝ ምላሽ ላይ የተሳተፉ እና እየተሳተፉ ያሉ የጤና ባለሙያዎቻችን፣ የዘርፉ አመራሮች፣ አጋር አካላት እና ሁሉም የሕብረተሰቡ ክፍል ምስጋና አቅርቧል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.