በመዲናዋ በተሽከርካሪ ጎማዎች ንግድ ተሰማርተው ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በመዲናዋ በተሽከርካሪ ጎማዎች ንግድ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ በተካሄደ የታክስ ኦፕሬሽን በ11 የንግድ ድርጅት ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የተሽከርካሪ ጎማ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ባካሄደው የኦፕሬሽን ተግባር ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 15 ግለሰቦችን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፡፡
ቢሮው ያካሄደው ድንገተኛ የኦፕሬሽን ተግባር ለረጅም ቀናት በተካሄደ ጥናት ላይ የተመሰረተ ሲሆን÷ በቁጥጥር ስር የዋሉት 15 ከፍተኛ እና መካከለኛ የመኪና ጎማ የሚሸጡ ነጋዴዎች ናቸው፡፡
ግለሰቦቹ የመንግስትን ግብር ለመሰወር ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ተገኝተው በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን የገለፀው ቢሮው ÷ የኦፕሬሽን ተግባሩ መርካቶን ጨምሮ በተመረጡ 12 የከተማዋ የጎማ መሸጫ ቦታዎች ላይ ነው የተከናወነው፡፡
ቢሮው የኦፕሬሽን ተግባሩን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ያካሄደ ሲሆን÷ ግለሰቦቹ በአሁኑ ወቅት የመንግሥትን ጥቅም ለማሳጣት ያለደረሰኝ ሽያጭ በመፈፀም ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፖሊስ ተይዞ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ተጠቁሟል፡፡
የኦፕሬሽን ተግባሩ በቀጣይ ቀናት በሌሎች ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተመላከተው፡፡
የንግዱ ማሕበረሰብ ግብይቶችን በደረሰኝ ብቻ እንዲፈፅም እና በ7075 ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም ወንጀሎችን እንዲያጋልጥ ተጠይቋል፡፡
FBC

6 months ago