Logo
Getu Temesgen
የዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን ለሜቄዶንያ አረጋውያን ማዕድ አጋራች! 🎄✨
#ethiopia | ​በአያት አካባቢ የሚገኘው የዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን፤ የፊታችን ረቡዕ የሚከበረውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በሜቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ለሚገኙ 500 አረጋውያን የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሂዳለች።

​📍 አዲስ ጉርብትና፡ አዲሱ የቤተክርስቲያኗ ሕንጻ ከሜቄዶንያ ማዕከል አጠገብ የሚገኝ ሲሆን፤ በገና ዕለት በይፋ አገልግሎት ከመጀመሩ አስቀድሞ እንደ ጎረቤት እና እንደ መንፈሳዊ ተቋም አረጋውያኑን ማሰብ ቅድሚያ ተሰጥቶታል።

​የማዕከሉ መስራች ክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ሌሎች ተቋማትም ይህን በጎ ተግባር እንዲጋሩ ጥሪ አቅርበዋል።

​"የተቸገሩትን ማሰብ እና ከጎናቸው መቆም ቤተክርስቲያን የተቀበለችው አደራ ነው።" 🙏

እዝራ እጅጉ ( ተወዳጅ ሚዲያ )
​#yugocitychurch #mekedonia #charity #ethiopianchristmas #genna #addisababa #ethiopia

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.