5 months ago
"የአእላፋት ዝማሬ" አዲስ አበባን አድምቋል፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ethiopia | በነገው ዕለት የሚከበረውን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና)ን በማስመልከት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደው ልዩ ሃይማኖታዊ መርሃ ግብር የከተማዋን ድምቀት ወደ ላቀ ደረጃ አድርሶታል።
🎶 የመስቀል አደባባዩ ድምቀት
በኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ አዘጋጅነት የተከናወነው “የአእላፋት ዝማሬ” በሺዎች የሚቆጠሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ምዕመናን የተሳተፉበት ሲሆን፣ መርሃ ግብሩ ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች ልዩ መንፈሳዊ ድባብን ፈጥሯል።
🎤 የከንቲባዋ መልዕክት
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሃ ግብሩ ላይ የታየውን ውበትና አንድነት በማድነቅ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት፦
"ዛሬ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተካሄደው 'የአእላፋት ዝማሬ' ድንቅ ነው። ከተማችንንም በጣም አድምቋል!" በማለት ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#የአእላፋትዝማሬ #የገናበዓል #አዲስአበባ #ኢትዮጵያ #አዳነችአቤቤ #መስቀልአደባባይ #ethiopianchristmas #addisababa #gena

🔴 አሁን በመስቀል አደባባይ! | የ2018 ዓ.ም "የአእላፋት ዝማሬ" ✨
#ethiopia | በገና ዋዜማ አዲስ አበባ በምስጋና እና በዝማሬ ድምፅ ደምቃለች
የ2018 ዓ.ም ታላቁ "የአእላፋት ዝማሬ" መርሐ ግብር በመስቀል አደባባይ እጅግ በደመቀ እና መንፈስን በሚያድስ "ሰማያዊ ድባብ" እየተካሄደ ይገኛል።
ነጭ የለበሰው ህዝበ ክርስቲያን አደባባዩን ሞልቶታል፤ የዝማሬው ድምፅም ያስተጋባል። እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!
📍 መስቀል አደባባይ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#meskelsquare #aelafzemare #genna #ethiopianchristmas #orthodox #live #addisababa #ethiopia

የዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን ለሜቄዶንያ አረጋውያን ማዕድ አጋራች! 🎄✨
#ethiopia | በአያት አካባቢ የሚገኘው የዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን፤ የፊታችን ረቡዕ የሚከበረውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በሜቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ለሚገኙ 500 አረጋውያን የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሂዳለች።
📍 አዲስ ጉርብትና፡ አዲሱ የቤተክርስቲያኗ ሕንጻ ከሜቄዶንያ ማዕከል አጠገብ የሚገኝ ሲሆን፤ በገና ዕለት በይፋ አገልግሎት ከመጀመሩ አስቀድሞ እንደ ጎረቤት እና እንደ መንፈሳዊ ተቋም አረጋውያኑን ማሰብ ቅድሚያ ተሰጥቶታል።
የማዕከሉ መስራች ክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ሌሎች ተቋማትም ይህን በጎ ተግባር እንዲጋሩ ጥሪ አቅርበዋል።
"የተቸገሩትን ማሰብ እና ከጎናቸው መቆም ቤተክርስቲያን የተቀበለችው አደራ ነው።" 🙏
እዝራ እጅጉ ( ተወዳጅ ሚዲያ )
#yugocitychurch #mekedonia #charity #ethiopianchristmas #genna #addisababa #ethiopia