የኪም ጆንግ ኡን ሚስጥራዊ ልጅ በሰሜን ኮሪያ የሥልጣን ተተኪ ልትሆን እንደምትችል የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ነው
ለወደፊት ሥልጣን ለመረከብ እየተዘጋጀች እንደሆነ የሚታመነው የሰሜን ኮሪያው መሪ የኪም ጆንግ ኡን ልጅ፣ የወደፊት ተተኪነቷ በይፋ ሊረጋገጥ ከሚችልበት ኩነት ቀደም ብሎ፣ በኩምሱሳን መካነ መቃብር ጉብኝት ወቅት ከወላጆቿ ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ታይታለች።
የሀገሪቱ የዜና ወኪል (KCNA) የለቀቃቸው ፎቶዎች እንደሚያሳዩት፣ ኪም ጆንግ ኡን ታህሰስ 23 ቀን ባደረጉት ጉብኝት ከባለቤታቸው ሪ ሶል-ጁ እና ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ታይተዋል።
በኩምሱሳን የፀሐይ ቤተ መንግሥት ዋና አዳራሽ ውስጥም ኪም ጁ-አይ በወላጆቿ መካከል ተቀምጣ ትታያለች።
የሰሜን ኮሪያ መሪ በዓመታዊ መታሰቢያዎች ወቅት ለሀገሪቱ መስራች አያታቸው ኪም ኢል-ሱንግ እና ለአባታቸው ኪም ጆንግ-ኢል ክብር ለመስጠት ኩምሱሳን ይጎበኛሉ።
ኪም ጁ-አይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ደጋግማ መታየቷ፣ እሷ አራተኛው ትውልድ አምባገነን መሪ ልትሆን ትችላለች የሚል ግምት በተንታኞች እና በደቡብ ኮሪያ የስለላ ተቋም ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል።
የሴጆንግ ኢንስቲትዩት ምክትል ፕሬዝዳንት ቼንግ ሴኦንግ-ቻንግ እንደተናገሩት፣ የጁ-አይ የመጀመሪያው የኩምሱሳን ቤተ መንግሥት ጉብኝት፣ ተተኪነቷ በይፋ ሊረጋገጥ በሚችልበት በሚቀጥለው የገዢው ፓርቲ ጉባኤ ዋዜማ በአባቷ የታቀደ እርምጃ ነው።
በኮሪያ ብሔራዊ አንድነት ኢንስቲትዩት የሰሜን ኮሪያ ባለሙያ የሆኑት ሆንግ ሚን በበኩላቸው፣ ሀገሪቱ በታላላቅ ኩነቶች ላይ የኪምን ባለቤት እና ልጅ በማሳየት "የተረጋጋ ቤተሰብ" እንዳላቸው ለመግለጽ ትፈልጋለች ብለዋል።
"ገና 13 ዓመቷ እንደሆነ የሚታመነውን እና የሰራተኞች ፓርቲን ለመቀላቀል እንኳን ዕድሜዋ ያልደረሰውን ኪም ጁ-አይን በይፋ ተተኪ አድርጎ መሾም በተግባር የማይቻል ነው" ብለዋል ሆንግ።
እንደ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፣ በ2010ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደተወለደች የሚታመነው ኪም ጁ-አይ፣ የዘንድሮውን የአዲስ ዓመት አቀባበል በዓል ላይ ተገኝታለች። ባለፈው መስከረም ወር ደግሞ ከመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉዞዋ ተደርጎ የሚቆጠረውን የቤጂንግ ጉዞ ከአባቷ ጋር አድርጋለች።
ሰሜን ኮሪያ እስካሁን የልጅቷን ዕድሜ በይፋ አላረጋገጠችም።

7 months ago