በስለናት "የቤተሰብ ፊልም ምሽት" ታህሳስ 25 ይካሔዳል!
የስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት የቤተሰብ የፊልም ምሽት ( Sele Enat Family Movie Night ) የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ10 ሰዓት ጀምሮ በበጎ አድራጎቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።
ይህ የፊልም ምሽት የስለናት ቤተሰቦች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የስለናት አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንዶች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው የሚታደሙበትና በጎ አድራጎተ ድርጅቱ ድጋፍ ከሚያደረግላቸው ሕፃናት ጋር ጥሩ የፍቅርና ቤተሰባዊ ጊዜን የሚያሳልፉበት ስለመሆኑ የስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ያሬድ አብዱ ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ጨምረው እንደገለፁት "በዚህ የፊልም ምሽት እንግዶች ልጆቻቸውን ይዘው በመምጣት በዕለቱ የተመረጠውን ፊልም አብሮ ከመመልከት ባለፈ በተቋሙ ሚታገዙት ህጻናት ፍቅርን በመስጠትና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ አጋርነትን የሚያሳዩበትና ቃልኪዳናቸውን የሚያድሱበት አይረሴ ምሽት ይሆናል!" ብለዋል።
አቶ ያሬድ አክለውም በዚህ የቤተሰብ የፊልም ምሽት በመታደም ለህፃናቱ ፍቅር በመስጠትና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ አጋር እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ስለናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከተመሰረተ 24 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በልዩ ልዩ ምክንያት ላጆቻቸውን ያጡ፣ ተጥለው የተገኙ እና በተለያየ ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ያለፉ ሕፃናትን ከመንግስት በመረከብ እና በመንከባከብ እንዲሁም ወደ ጎዳና የወጡ ሕፃናትን መልሶ ወደ ቤተሰብ በማቀላቀል በከፋ ድህነት ውስጥ ላሉ ሕፃናት የቤተሰቦቻቸውን አቅም በመገንባት በተለያዩ አማራጭ የድጋፍ አይነቶች ውስጥ በማካተት በአዲስ አበባና በሻሸመኔ እስካሁን ከ11ሺህ በላይ ሕፃናትን እና እናቶችን መታደግ ችሏል።
"የተሻለ የልጅነት ጊዜ ለሁሉም ሕፃናት!" በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው ስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት በአሁኑ ሰዓት ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎችም አማራጮች ለ1 ሺህ 700 የተለያዩ ሕፃናት እና ሴቶች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ማህበረሰቡ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በሙያና በጉልበት ለድርጅቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ያሬድ አብዱ ጥሪ በማቅረብ
ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም በ0901668822/ 0921939393/ 0940656565 በመደወል ወይም በድርጅቱ ቅጥር ግቢ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

7 months ago