Logo
FIDEL POST NEWS
ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ ደምን፣ ሕይወትን እና ሞትን ተጋርተዋል ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን ተናገሩ

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተላለፉት የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ሰሜን ኮሪያና ሩሲያ በዩክሬኑ ጦርነት ውስጥ "የደም፣ የሕይወት እና የሞት" ትስስር አላቸው ብለዋል።

​ በሰሜን ኮሪያ የዜና ወኪል በታተመው በዚህ መልዕክት፤ ኪም 2025 በፒዮንግያንግ እና በሞስኮ መካከል ያለው ጥምረት "በአንድ ቦይ ውስጥ በጋራ በፈሰሰ ደም፣ በሕይወት እና በሞት" የጠነከረበት "በእውነትም ትርጉም ያለው ዓመት" ነው ብለዋል።

የደቡብ ኮሪያ እና የምዕራባውያን የስለላ ድርጅቶች ፒዮንግያንግ በዩክሬን ጦርነት ከሞስኮ ጎን ተሰልፈው እንዲዋጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን መላኳን ቀድመው ዘግበው ነበር። ሰሜን ኮሪያ ባለፈው አመት ሚያዚያ ወር ላይ ወታደሮቿ የሩሲያን ወታደራዊ ዘመቻ ለመደገፍ መሰማራታቸውን እና አንዳንዶቹም በውጊያው ላይ መገደላቸውን አረጋግጣለች።

​በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ፒዮንግያንግ በነሐሴ ወር ውስጥ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የኩርስክ ክልል ፈንጂዎችን ለማጽዳት ወታደሮችን ልካ እንደነበር አምናለች።

ወታደራዊ ክፍሉ ወደ ሀገር ሲመለስ ታህሳስ 4 ቀን ኪም ባደረጉት ንግግር፥ በ120 ቀናት ቆይታቸው ቢያንስ ዘጠኝ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች መገደላቸውን ተናግረዋል።
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.