ኪም ጆንግ ኡን ለጦርነት ዝግጁነት የሚውሉ ሚሳይሎች በከፍተኛ መጠን እንዲመረቱ አዘዙ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ሊሰነዘርባት የሚችለውን ማንኛውንም ወታደራዊ ጥቃት ለመመከትና እንደ "ጦርነት መከላከያ" የሚያገለግሉ ሚሳይሎች በከፍተኛ መጠን እንዲመረቱ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፈዋል።
መሪው ይህንን ትዕዛዝ የሰጡት ዋና ዋና የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎችን በጎበኙበት ወቅት እንደሆነ የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የኪም ጆንግ ኡን ጉብኝት ትኩረት ያደረገው ስልታዊ ሚሳይሎችን፣ የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን እና ሌሎች የጦር ሜዳ መሣሪያዎችን በሚያመርቱ ተቋማት ላይ ነው። መሪው በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት፣ ሰሜን ኮሪያ ጠላቶቿን ሊያስደነግጥ የሚችል እጅግ ዘመናዊና ግዙፍ ወታደራዊ አቅም መገንባት ይኖርባታል።
ይህ የጦር መሣሪያ ምርት ማሳደጊያ እቅድ ሀገሪቱ ማንኛውንም የጠላት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመመከትና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም አጥቂ ኃይሎችን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የሚያስችል ዝግጁነት እንዲኖራት ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ እንቅስቃሴ የተጀመረው አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በጋራ የሚያካሂዱትን ወታደራዊ ልምምድ ተከትሎ እንደሆነ ይገመታል። ሰሜን ኮሪያ እነዚህን የጋራ ወታደራዊ ልምምዶች ለወረራ እንደታቀዱ የዝግጅት እርምጃዎች አድርጋ ስለምትመለከታቸው፣ የሚሳይል ምርቷን ማሳደጓ ለነዚህ እንቅስቃሴዎች የሚሰጥ ምላሽ መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ።
በተጨማሪም ኪም ጆንግ ኡን በፋብሪካዎቹ በነበራቸው ቆይታ፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በጦር መሣሪያ ምርት ላይ እንዲካተቱ እና የማምረት አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የላቁ የኢንጂነሪንግ ስራዎች እንዲከናወኑ አሳስበዋል። ይህ የፒዮንግያንግ አቋም በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለውን ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተሰግቷል።
አለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም የምዕራባውያን አገራት የሰሜን ኮሪያን የሚሳይል ምርት ማሳደግ እና ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አጥብቀው እያወገዙ ይገኛሉ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለው ማዕቀብ አሁንም እንደቀጠለ ቢሆንም፣ ሀገሪቱ ግን የሚሳይል እና የኒውክሌር ፕሮግራሟን ከማስፋፋት ወደኋላ አላለም።
#menaharia_fm

8 months ago