Logo
SeledaPost
እንግሊዝ የማርበርግ ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ ድጋፍ አደረገች

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስዳባ በርክክቡ ሥነ ሥርዓት ላይ የእንግሊዝ መንግሥት ላደረጋቸው ወቅታዊ ድጋፎች አመስግነዋል።

ልገሳው ድንበር አቋርጠው የሚመጡ በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ለመዋጋት እናየጤና ተቋማት ለሕዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ የመስጠት አቅምን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተናግረዋል።

መሣሪያዎቹ በወረርሽኝ ምላሽ ጥረቶች ውስጥ የተሳተፉ ግንባር ቀደም የጤናባለሙያዎችን ለመጠበቅ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የዩኬ አምባሳደር ዳረን ዌልች በበኩላቸው ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያየሕክምና መሳሪያዎችን በማምረት ረገድ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ትደግፋለች ብለዋል።

የሁለቱ ሃገራት ትብብር ከኢትዮጵያ አልፎ ለአህጉራዊ እና ለዓለም አቀፍ የጤናደህንነት አስተዋጽኦ ያደርጋል ማለታቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ድጋፉ የግል መከላከያ መሳሪያዎችን (PPE) እና ወሳኝ የምርመራ ኪቶችንያካተተ ሲሆን፥ ይህም የኢትዮጵያን የወረርሽኝ መከላከል ዝግጁነት እና ምላሽ ለማሻሻል ያግዛል ተብሏል።

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.