Logo
Getu Temesgen
በሳውዲ አረቢያ በአንድ ዓመት ውስጥ ቢያንስ በ347 ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት ተግባራዊ ተደረገ
#ethiopia | ሳውዲ አረቢያ ለተከታታይ ሁለተኛ አመት በየአመቱ በሚፈጸሙ የሞት ቅጣት በመጨመር ቀድሞ የተያዘው ሪከርድ ላይ ብልጫ አሳይቷል።

በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድን የሚከታተለው እና የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸው ሰዎች መረጃ የሚያገኘው ሪፕሪቭ የተባለው መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ቡድን እንዳስታወቀው በ2024 ከነበረው 345 የሞት ቅጣት በዚህ አመት ቢያንስ በሁለት ሰዎች ጨምሮ 347 ሰዎች ተገድለዋል።

ይህ “ክትትል ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሳዑዲ ውስጥ ውስጥ እጅግ ደም አፋሳሽ የሞት ፍርድ የተካሄደበት ዓመት ነው” ብሏል። በቅርቡ የተገደሉት እስረኞች ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች የተከሰሱ ሁለት የፓኪስታን ዜጎች ናቸው።

ሌሎች በዚህ ዓመት የተገደሉት ጋዜጠኛ እና ሁለት ወጣቶች ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ ወንጀሎች ሲሆን ህጻናት እና አምስት ሴቶች ላይ እርምጃው ተግባራዊ ሆኗል።

ከሞት ቅጣቱ ጋር በተያያዘ ወደ ሁለት ሶስተኛው ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ተፈርዶባቸዋል፤ ይህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት “ከአለም አቀፍ ደንቦች እና ደረጃዎች ጋር የማይጣጣም ነው” ሲል አስታውቋል።

በአደንዛዥ እፅ የሞት ቅጣት ተግባራዊ ከሆነባቸው ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የውጭ ሀገራት ዜጎች ናቸው። የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት የሞት ቅጣት መጨመሩን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
#bisratfm

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.