Logo
YenetaTube
የስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 54 የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በ2018 የመጀመሪያ አምስት ወራት (ህዳር 30/2018 ዓ.ም ድረስ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዲጂታል የሙስና መረጃ (ጥቆማ) መቀበያ ስርዓት እና በሌሎች አማራጮች ከቀረቡ ጥቆማዎች ውስጥ 54 አመራርና ሰራተኞች ጥፋተኛ መሆናቸውን ተረጋግጦ እርምጃ ተወሰደ።

ተቋሙ ተግባራዊ ባደረገው የዲጂታል ሙስና ጥቆማ ማቅረቢያ በቀረቡት ጥቆማዎች መሰረት በአምስቱ ወራት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰራተኞች መካከል 10 የፅሁፍ፣ 37 የደመወዝ፣ 2 ከቦታ የማንሳት፣ 5 ስንብት በድምሩ በ54 ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

ከስራ እንዲሰናበቱ የተደረጉት ሰራተኞች በስነ ምግባር ጥሰት ምክንያት ሲሆን፤ ይህም የጥቆማ መቀበያ ስርዓቱ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ደንበኞች የሚሰጡት ጥቆማ ዋጋ ያለው መሆኑን እና የሚታዩ ብልሹ አሰራርን ለመታገል ተቋሙ እያደረገ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡

ተቋሙ ከደንበኞች የሚቀርቡ ጥቆማዎችን ተቀብሎ በማጣራት አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት ያስችለው ዘንድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ አስፈላጊ ሲሆን፤ የዲጂታል የጥቆማ መቀበያ ስርዓቱን በመጠቀም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የመስናና ብልሹ አሰራር ችግሮች ላይ ጥቆማዎችን እንዲያቀርቡ ያበረታታል፡፡

በአምስቱ ወራት የብልሹ አሰራር ጥቆማ ከቀረበባቸው የስራ ሂደቶች መካከል የአዲስ ኃይል ጥያቄ፣ የኃይል መቆራረጥና አስቸኳይ ጥገና፣ የቆጣሪ ንባብና የቢል ስብሰባ፣ የንብረት አያያዝና አጠቃቀምና ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡

ተቋማችን በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዮ የመልካም አስተዳደር ችግርና ብልሹ አሰራርን ለመታገልና እርምጃ ለመውሰድ አሁንም ቁረጠኛ መሆኑን እየገለፀ፤ ተገልጋዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት መሰል ችግሮችን ሲመለከቱ በተዘረጋው ዘመናዊ የሞባይል መተግበሪያ ወይም በበየመረብ ገፅ (www.eeuethics.et) በመጠቆም የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.