Logo
SeledaPost
ከዘጠኝ ቀናት ቆይታ በኋላ በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው መገኘቱን ሪፖርት ተደርጓል።

ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በተደረጉ ምርመራዎች ምንም አይነት አዲስ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዘ ሰው ሪፖርት ሳይደረግ ከቆየ በኋላ በዛሬው ዕለት አንድ ሰው የማርበርግ ቫይረስ ተጠቂ ሆኖ መገኘቱን ዕለታዊ የምርመራ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

የጤና ሚኒስቴር በጂንካ ከተማ የተከሰተው ወረርሽኝ የማርበርግ ቫይረስ ሆኖ መገኘቱን ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን ያወጀው ህዳር 5/2018 ዓም በሰጠው መግለጫ ነበር።

ወረርሽኙ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን የመመርመር፣ የመለየት እና የማከም ስራዎች እየተሰሩ የሚገኝ ሲሆን በየዕለቱ በሚከናወኑ ምርመራዎች አዲስ በቫይረሱ የተጠቁ፣ ህይወታቸው ያለፈ፣ ያገገሙ እንዲሁም በህክምና ላይ የሚገኙ ታካሚዎችም ይፋ እየተደረጉ ይገኛል።

ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በርካታ ምርመራዎች ቢደረጉም ምንም አይነት የማርበርግ ቫይረስ ተጠቂ ሳይገኝ ቆይቶ የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት አንድ ሰው የቫይረሱ ተጠቂ ሆኖ መገኘቱን ዕለታዊ የምርመራ ሪፖርቱ ያሳያል።

በዛሬው ዕለት በተከናወኑ 56 ምርመራዎች ውስጥ አንድ ሰው ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ያመለክታል።

በአጠቃላይ እስካሁን 1765 ምርመራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ በ14 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

በቫይረሱ ሳቢያ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 4 ሰዎች ደግሞ አገግመው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀል ችለዋል።

በአሁኑ ሰአት ህክምና በመከታተል ላይ የሚገኙት 2 ታካሚዎች ናቸው።

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.