Logo
Getu Temesgen
‎"በቫይረሱ ስርጭት ስጋት ምክንያት በዓሉ በአደባባይ አይከበርም " - የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ
#ethiopia | ‎የአሪ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ "ዲሽታ ጊና" በዓል በማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ስጋት ምክንያት ዘንድሮ እንደማይከበር የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

‎በብሔረሰቡ ዘንድ የአብሮነት ፣ የዕርቅና የሠላም፣ የመረዳዳትና የአዲስ ዘመን ብስራት ወቅት ተደርጎ የሚወሰደዉ ይህ በዓል በየዓመቱ በታህሳስ ወር መግቢያ በታላቅ ድምቀት ይከበር እንደነበር አስታውሰዋል።

ዘንድሮ ግን በአከባቢዉ ተከስቶ ለሰዎች ሞት ምክንያት በሆነዉ የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ስጋት ምክንያት በዓሉ ታስቦ ብቻ እንዲዉል ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከባህል አባቶች ጋር ከመግባባት መደረሱን ገልፀዋል።

‎በዓሉን በዓለም አቀፉ የትምህርት ሳይንስና ባህል ጥበቃ ድርጅት ዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረቶች መጀመራቻቸዉን ያነሱት አቶ አብረሃም ሕዝቡ ዘንድሮ በዓሉን እሴቱን በወል እያሰበ በዓሉን በታሳቢነት እንዲያከብረዉ ጥሪ አቅርበዋል ያለው ቲክቫህ ነው።

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.