Logo
Getu Temesgen

ጋዳፊ፣ “ሀገሬ ባሕር በር ተነጥቃ እንድትቀጥል አልፈቅድም የሚል ኢትዮጵያዊ ይመጣል..!”
—> “የኤርትራ ነፃነት በኢትዮጵያ ባህር በር አልባነት ላይ ሊዘልቅ አይችልም”
#ethiopia | የኤርትራ ነፃነት ሲሳካ ኢትዮጵያን የባህር በር አልባ አድርጓታል፣ ወደ ባህር የሚያደርስ ሌላ አማራጭ ሳይኖራት የኢትዮጵያን የውሃ ደጃፏ እንደዘጋባት ነው (እኔ) የምገልፀው። ታዲያ ይህ ሁኔታ ባለበት ሊዘልቅ በፍፁም አይችልም፣ ጊዜያዊ ተጨባጭ ነው ሊሆን የሚችለው። በበኩሌ ሁልጊዜም እነግራቸው ነበር - ለኤርትራ ነፃነት ሰጥታ አገሪቱ እንደገና የባህር በር እንዲዘጋባት ዋጋ የከፈለችበት ተጨባጭ ባለበት እንዲቀጥል የሚፈቅድ ኢትዮጵያዊ ሊኖር አይችልም’ እላቸው ነበር። የኤርትራ ነፃነት በኢትዮጵያ ባህር በር አልባነት ላይ ሊዘልቅ አይችልም።

(እናንት..አሁን ላይ ወንድማማችና አጋር ጎረቤቶች ነን ትሉናላችሁ፣ ይሄ ማሻአላህ ነው፣ እናንተ አሁን ተስማምታችሁ ልትቆዩ ትችሉ ይሆናል። ነገርግን በኢትዮጵያ ሌላ ትውልድ እንደሚመጣ ልብ በሉ፣ ይህ የማይቀር ነው። ያን ጊዜ አገሬ ከባህር ተዘግታ፣ የባህር በር አልባ አትሆንም የሚል ኢትዮጵያዊ ይመጣል፣ …እስከዚያው ነው…።

#የዓባይልጅ

📹ቪዲዮ፣ የቀድሞ ሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ በፈረንጅ 1998 ካደረገው ንግግር፣ የአረብ ማህበራዊ ሚዲያውን ስሞነትር ያገኘሁት
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.