Logo
YenetaTube
ናይጀሪያ የሳህል ግዛትን አየር ክልል ተዳፍራለች !/ ቡርኪናፋሶ /

ቡርኪናፋሶ የአየር ክልሏን ጥሰት በመፈጸም በበረራ ላይ የነበረው የናይጄሪያ ወታደራዊ አውሮፕላንና የበረራ ቡድን በቁጥጥር ስር ማዋሏን መናገሯ ተሰማ ።

ድርጊቱ የናይጄሪያ ተዋጊ ጄቶች በአጎራባች ቤኒን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን በማፍረስ ወሳኝ ሚና እንደተጫወቱ ከተዘገበ ከአንድ ቀን በኋላ መፈፀሙ የሳህል አጋሮች ዘንድ ቁጣን አስነስቷል ተብሏል ።

የቡርኪና ፋሶ መንግስት 11 ወታደራዊ አባላትን የያዘ የናይጄሪያ አየር ኃይል C-130 አውሮፕላን ያለ ፈቃድ ወደ አገሪቱ የአየር ክልል ከገባ በኋላ ሰኞ ዕለት እንዲያርፍ ተገዷል ብሏል።

በጥር ወር ከክልላዊው ማኅበረሰብ ECOWAS ራሳቸውን በማግለል የራሳቸውን የሳህል ግዛቶች ጥምረት የመሰረቱት ማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ በጋራ ሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ የናይጄሪያ ወታደራዊ አውሮፕላን በቡርኪናፋሶ የአየር ጥሰት መፈፀሙንና በድንገት ቦቦ-ዲዮላሶ አካባቢ መገኘቱን አውግዘዋል፣ በአየር ክልላቸው ላይ በሚፈጸሙ ጥሰቶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ አስፈራርተዋል።

የሳህል ሀገራት ጥምረቱ ታህሳስ 8፣ 2025 የናይጄሪያ ፌዴራል ሪፐብሊክ የአየር ኃይል ንብረት የሆነው C-130 አውሮፕላን ከሀገሪቱ ምንም አይነት ፍቃድም ሆነ ይሁንታ ሳያገኝ 11 ወታደራዊ ሰራተኞችን ይዞ በድንገት በቡርኪና ፋሶ መገኘቱን "ከመደበኛ የደህንነት ሂደቶች እና ከአለም አቀፍ የአቪዬሽን ፕሮቶኮሎች" ጋር የሚጣረስ ድርጊት ከመሆኑም በላይ ነገር ፍለጋ ነዉ ሲሉ በጋራ መግለጫው ተናግረዋል።

ተግባሩንም "ወዳጃዊ ያልሆነ ድርጊት" ሲሉ የጠሩት ሀገራቱ ከዚህ በኋላ የአገሮቹ የአየር ኃይሎች ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጣቸዉ የኮንፌዴሬሽኑን የአየር ክልል ጥሶ የተገኘ ማንኛውንም አውሮፕላን "ጥቃት ለማድረስ" ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል። ብለዋል ።

ሶስቱ የሳህል አገሮች፣ በአንድ ወታደራዊ አገዛዝ ሥር በመሆን ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የጂሃዲስት አማፂያን እየተዋጉ ባሉበት ወቅት
እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ የቀድሞዋ ቅኝ ገዥ ፈረንሳይና የቀጠናውን ሀብት የበዘበዙ ምዕራቡ ዓለም ሴራ ሊኖርበት እንደሚችል ገልፀዋል ።

የቡርኪናቤ ደህንነት ቢሮ ባደረገው የመጀመሪያ ምርመራ አውሮፕላኑ በአገሪቱ ላይ ለመብረር ፈቃድ እንደሌለውና የተፈፀመው ኤኢኤስ የአባል አገራትን ሉዓላዊነት መጣስ እንደሆነ ዳግም ለመሞከር ቢታሰብ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የአየር መከላከያ ስርዓቶቹ በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።ሲሉ በሦስቱ የምዕራብ አፍሪካ አገራት የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል ።

ይሁን እንጂ የናይጄሪያ አየር ኃይል ከሌጎስ የተነሳው አውሮፕላን ወደ ፖርቱጋል "የጀልባ ተልዕኮ" ላይ እንደነበር ተናግሯል፣ ነገር ግን በ"ቴክኒካል ስጋት" ምክንያት በቡርኪና ፋሶ አቅራቢያ ወደሚገኘው መስክ "የጥንቃቄ" ለማረፍና የደህንነት እርምጃ ለመውሰድ ወስኗል። ሲል ግልፅ ያልሆነ ማስተባበያ ሰጥቷል ።

ለዘገባዉ የሶስቱ ሀገራት የመንግስት ሚዲያዎችና አፍሪካ ኒዉስን ተጠቅመናል ።

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.