የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል የሙከራ ክትባት መስጠት ተጀመረ
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ለመከላከል የሚያስችል ክትባት በደቡብ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ክልል በተመረጡ አከባቢዎች ለፈቃደኛ ተሳታፊዎች መስጠት ተጀምሯል።
ክትባቱ በዓለም ዙሪያ በተደረጉ ቅድመ ጥናቶች ደህንነቱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ከአንድ አመት በፊትም በሩዋንዳ በተከሰተው ተመሳሳይ የማርበርግ በሽታ ጥቅም ላይ ዉሎ በሽታውን ለመከላከል ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን አሳይቷል፡፡
ክትባቱ በቅድሚያ ተጋላጭ ለሆኑ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም በቫይረሱ ተይዘው ከነበሩ ሰዎች ጋር ግንኙነት ለነበራቸው በፈቃደኝነት የሚሰጥ ሲሆን ሂደቱም በዓለም ጤና ድርጅት እና በኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን መመሪያዎች መሰረት ደረጃውን ጠብቆ ይከናወናል፡፡
Via Ministry of Health

6 months ago