Logo
SeledaPost
የሙከራ ክትባት መስጠት ተጀምሯል

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ የሙከራ ክትባት በደቡብ ኢትዮጵያና ሲዳማ ክልል በተመረጡ አካባቢዎች ለፈቃደኛ የሙከራ ተሳታፊዎች መስጠት ተጀምሯል።

ክትባቱ በዓለም ዙሪያ በተደረጉ ቅድመ ጥናቶች ደህንነቱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ከአንድ አመት በፊትም በሩዋንዳ በተከሰተው ተመሳሳይ የማርበርግ በሽታ ጥቅም ላይ ዉሎ በሽታውን ለመከላከል ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን አሳይቷል፡፡

ክትባቱ በቅድሚያ ተጋላጭ ለሆኑ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም በቫይረሱ ተይዘው ከነበሩ ሰዎች ጋር ግንኙነት ለነበራቸው በፈቃደኝነት ለሙከራ ጥናቱ ተሳታፊዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ሂደቱም በዓለም ጤና ድርጅትና በኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን መመሪያዎች መሰረት ደረጃውን ጠብቆ እንደሚከናወን ታውቋል፡፡

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.