Logo
Getu Temesgen
በጢሙ ፊደል አስቆጣሪው
#ethiopia | በወል ትስስር ገጾቻቸው ትኩረት፣ ዕይታን ፍለጋ ሰዎች ምንም ከማድረግ የሚመለሱ አይመስለንም ያሉት የኤን ዲ ቴቪ ዘጋቢዎች እንግሊዛዊው ሰውዬም እንዲሁ ነው ብለውናል፡፡

በገጽ ሥሙ ሞቬምበር ዩኬ የተሰኘው ግለሰብ አንድ ዕለት በወል መገናኛ ትስስር ገጹ ካሜራውን ደግኖ ቀረበ፤ ከዚያም ጺሙን በእንግሊዘኛው A ፊደል ቅርጽ ከረከመው፡፡

እንዲህ እያለ በተከታታይ ሙሉ የእንግሊዘኛ ፊደል ተራን ቅርጽ ጺሙን እየተቆረጠም ከ2.5 ሚልየን በላይ ተከታዮችን እንዳፈራ ኤን ዲ ቴቪ አስነብቧል፡፡

ግለሰቡ ይህን ማድረጉ ያስደነቃቸው ተከታዮቹ ሰውዬው በአንድ ፊደል ቅርጽ ተከርክሞ፣ እንደገና ጺሙ እስኪበቅል መጠበቅና፣ ዳግም በሌላ ፊደል ቅርጽ ለመከርከም ያሳየውን ቁርጠኝነት ‹‹ጀግናስ እንዳንተ ያለው እንጂ›› የሚል ዓይነት ሙገሳ ከማዥጎድጎዳቸው ባለፈ፣ ‹‹ምን ያህል ጊዜ ፈጀብህ?›› እያሉ የጠየቁም እንዳሉ በዜናው ላይ ተጠቅሶ አስተውለናል፡፡
#tirtafm

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.