Logo
FastMereja
አርቲስት ሐመልማል አባተ እና አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ በAFFA አዋርድ ሊሸለሙ ነው።
#fastmereja I ኔክስት ፋሽን ዲዛይን ‎ኮሌጅ ከተመሰረተ 20 አመት መሙላቱን እንዲሁም የAFFA award ምክንያት በማድረግ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።

በዲሊኦፖል ሆቴል በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የኮሌጁ የ20አመታት ጉዞ፣ የፋሽን ሾው እና የAFFA ውድድርን በተመለከተ ገለፃ አድርጓል።

በመግለጫውም የAFFA ተሸላሚዎች ይፋ የተደረጉ ሲሆን

‎📌 ሳምራዊት መርስኢሀዘን - ከሳምራ ሌዘር (በኢንተርናሽናል ደረጃ የኢትዮጵያን ሌዘር በማስተዋወቅ)

📌 አርቲስት ሐመልማል አባተ (ፋሽንና የባህል አልባሳትን ለረጅም ጊዜ በመልበስና በማስተዋወቅ ዲዛይነሮችን በማገዝ)

📌 ዮሐንስ ታጠቅ- ጆኒ ቪዲዮ (ዲዛይነሮችና ሞዴሎችን ላለፉት 30 አመታት ፎቶ በማንሳት)

📌 አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ (ፋሽንና የባህል አልባሳትን ለረጅም ጊዜ በመልበስና በማስተዋወቅ ዲዛይነሮችን በማገዝ)

📌 አርክቴክት ቃልኪዳን ታደሰ (ለ15 አመታት በባህላዊ የሽመና ጨርቆች ቤትን በማስዋብ)

📌 ሄኖክ ሲሳይ -ከሄኒ አፍሮ (ሞዴሎችን በበጎ ፈቃደኝነት ሜካፕና ፀጉር በመስራትና ብዙ ዲዛይነሮችን በመደገፍ)

📌 የፋሽን ዲዛይነር እና አርክቴክት ሜቲ ሀይለማርያም (ክርኤቲቭ ያንግ ዲዛይነር)

📌 ፎዚያ እንድሪስ የኢትዮዽያ የባህል አልባሳትን እለት እለት እንዲለበስ በማድረግ በመላው አለም እንዲታወቅ በማድረግ (ክርኤቲቭ ያንግ ዲዛይነር) ናቸው።

ኔክስት ፋሽን ዲዛይን በ2004 እ.ኤ.አ በዲዛይነርና ሞዴል ሳራ መሀመድ በሞዴሊንግ ስልጠና የተመሰረተና ስራውን ጀመረ።

ኮሌጁ ላለፉት 20 ዓመታት በመደበኛው የሥልጠና ፕሮግራም ከ5200 በላይ እንዲሁም በአጫጭር የስልጠና ዘርፍ ከ1000 በላይ ብቃት ያላቸው ስመጥር የሆኑ ዲዛይነሮችን በፋሽን ዲዛይን አሰልጥኖ በማስመረቅና ኢንደስትሪውን እንዲቀላቀሉ በማድረግ በዘርፉ ያለውን ትልቅ ክፍተት እየሞላ ያለ ኮሌጅ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አሰልጥኖ ካስመረቃቸውም መካከል ሰላሳ በመቶ የሚሆኑት ሴት ሰልጣኞች ሙሉ በሙሉ በኮሌጁ ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝተው የሰለጠኑ ናቸው፡፡

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.