Logo
Getu Temesgen
ኪም ጆንግ ኡን ፕሪሚየር ሊጉ በሀገራቸው እንዲታይ ፈቃድ ሰጡ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሀገራቸው እንዲተላለፍ ፈቃድ መስጠታቸው ይፋ ሆኗል።

ጨዋታዎቹ የቀጥታ ስርጭት እንዳያገኙ ቀድመው እገዳ ጥለው የነበሩት ኪም አሁን ፈቃድ ሰጥተዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች አሁንም ቢሆን በቀጥታ ስርጭት ሳይሆን የማያስፈልጉ ጉዳዮች እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ይተላለፋሉ ተብሏል።

ኪም ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ በሊጉ የሚጫወቱ የደቡብ ኮሪያ ተጫዋቾች በፍጹም መታየት የለባቸውም።

የብሬንትፎርዱ ኪም ጂሶ እና እና የዎልቭሱ ህዋንግ ሂ ቻን በሊጉ የሚገኙ ብቸኛ የደቡብ ኮሪያ ተጫዋቾች ናቸው።

የ90 ደቂቃ ፍጆታ ያለው አንድ ጨዋታ ወደ 60 ደቂቃ እንዲያጥር ተደርጎ ለተመልካች እንደሚደርስም ይፋ ሆኗል።
#ebc

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.