"የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህጻናት የመጡ ኮምፒዩተሮች ጉሙሩክ ይዞብናል" ~ ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት
* ለአገርና ለሕዝብ ጥሪ አቀርበዋል
#ethiopia | በዛሬው ዕለት የድርጅቱ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ( Goodwill Ambassador )የሆነችው አትሌት መሰረት ደፋር እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አርቲስቶች፣ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት በትንቢተ ኤርምያስ እና ስብስቴ ነጋሲ ትምሕርት ቤቶች ጉበኝት አካሂደዋል።
የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዶክተር ጽጌ ጥበቡ፣ "እነዚህ ልጆች ከቀለም ትምሕርቱ ይልቅ ይበልጥ የሚጠቅማቸው የሞያ ትምሕርት ቢማሩ ነው። ውጤታማም ይሆናሉ" በሚል መነሻ ሃሳብ የትምሕርት ቤት የደንብ ልብስ፣ ሥዕል የሚስሉባቸውን ቀለማትና መሰል ግብዓቶችን በማቅረብ ረገድ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
አያይዘውም ለሕጻናቱ የልዩ ፍላጎት ባለሞያዎችን በመመደብ እና በመምሕራኑ ትብብር ጥናት በማስጠናት፣ እነዚሁ ሕጻናት የሽመና ማሽን ተገዝቶላቸው ውብ የሸማ ውጤቶችን ሰርተው እስከማቅረብ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
ድርጅቱ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የእእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ወጣቶች በሸማ ሙያ፣ በኮምፒውተር (ኮዲንግ)፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ሥዕል፣ በስፖርት እና በሌሎችም ዘርፎች እያሰለጠነ ይገኛል።
ዶ/ር ጽጌ እንዳወሱት በዚህም የት/ቤት የደንብ ልብስ፣ ሥዕል የሚስሉባቸውን ቀለማትና መሰል ነገሮችን በማቅረብ የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎችና በመምህራኑ ትብብር ጥናት በማስጠናት የሽመና ማሽን ተገዝቶላቸው የሚያማምር ሸማ ሰርተው እስከ ማቅረብ ደርሰዋል ብለዋል።
የአእምሮ እድገት ውስንነትና ሌሎች የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህፃናትና ወጣቶች በመንፈሳዊ፣ ስሜታዊ፣ ትምህርታዊና ሙያዊ ፕሮግራሞች በመደገፍ ላይ ናቸው።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት አትሌት መሰረት ደፋርን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ( Goodwill Ambassador ) አድርጎ መሾሙንም በአሜሪካን ሀገር በተደረገ ሥነ ስርዓት ተከናውኗል።
ድርጅቱ ከአትሌት መሰረት ደፋር ጋር የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ስምምነት ያደረገው ድርጅቱ ህዝቡ ጋር የነበረውን ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ለማጎልበት የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት እንደሆነ ተነግሯል።
ጀግናዋ አትሌት መሰረት ደፋር እንደተናገረችው የእነዚህ ህጻናት ጉዳይ የሁሉም ሀላፊነት ነው ብላለች። በህጻናት ህይወት ላይ መስራት ሀገር ከመስራት እኩል ነው ስትልም አጽንኦት ሰጥታ ተናግራለች።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት እ.ኤ.አ በ 2007 ዓ.ም ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ አገር ኑሮ ባደረጉት በዶ/ር ጽጌ ጥበቡ ተመሰረተ፡፡
ከየካቲት 09 ቀን 2014 ዓ/ም በበጎ አድራጎት
በአዋጅ ቁጥር 11/03/2011 መሠረት በመዝገብ ቁጥር 6067 በኢ.ፊ.ዲ.ሪ. የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት ተሰጥቶት የሰሜን አሜሪካውን ተሞክሮ ለማስፋፋት እየሰራ ያለ ( በጎ ሥራው ያልተነገረለት) ተቋም ነው፡፡
ራዕይ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ያስመጣኋቸው የኮምፒዩተር መሳሪያዎች ጉምሩክ ላይ ተይዘውብናል ሲሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ራዕይ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ከአገር ውጭ ያስመጣቸው የኮምፒዩተር መሳሪያዎች ጉምሩክ ይዞብናል ብሏል።
እነዚህ ልጆች የኮምፒዩተር ስልጠና እንዲወስዱ የኮምፒዩተር መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ለማስገባት እየተሰራ ቢሆንም መሳሪያዎቹ ጉምሩክ ላይ በመያዛቸው ልጆቹ እስካሁን የኮምፒዩተር ስልጠና ሊወስዱ አልቻሉም ለዚህም የሚመለከተው አካል ችግሩን እንዲቀርፍ ለአገርና ለሕዝብ ጥሪ አቀርበዋል።
ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪም የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሌሎች ህጻናቶች ለመደገፍና ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንዲሁም ተጨማሪ ስራዎቹን ለማከናወን የቦታ እጥረት እንዳለበት የገለጸ ሲሆን የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቋል።
በዛሬው የመስክ ዝግጅት ላይ የተገኙት ወላጆችም ሲቃ በተሞላበት ስሜት ሆነው ተቋሙን ያመሰገኑ ሲሆን እንደስምሽ መሰረት ለልጆቻችን መሰረት ሁኚልን ብለዋል።
ራዕይ ልጆቻችንን ቢቻ አይደለም የሚደግፈው እኛንም በየወሩ ገንዘብ እየሰጠን ኑሮአችንን እንዲሻሻል አግዞናል ብለዋል።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት በ7 ት/ቤት ከ300 በላይ ለሚሆኑ ልጆች ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን በዛሬው እለትም ድጋፍ ከሚያደርግባቸው ት/ት ቤቶች ውስጥ በትንቢተ ኤርሚያስና በስብስቴ ነጋሲ ት/ቤቶች የሚማሩ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች የሚሰሯቸውን የሙያ ስራዎች ጉብኝት ተካሄዷል።
በተጨማሪም ሌሎች ልጆችንም በሙያ ለመደገፍ የቦታ እጥረት ስላለ የሚመለከተው አካል ይህንንም ችግር እንዲመለከት ጥሪ አቀርበዋል።
በመላው አገሪቱ ባሉ ሁለም ት/ቤቶች ልዩ ፍላጎቶች ያላቸው ልጆች ትኩረት ተሰጥቷቸው፣ የሙያና የህይወት ክህሎት ስልጠና አግኝተው ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ አላማው ያደረገው ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት በዶክተር ፅጌ አማካኝነት በኢትዮጵያ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት ተልዕኮ የአእምሮ እድገት ውስንነትና የእድገት መዘግየት ላለባቸው ልጆች የስነልቦና እና የሙያ ክህሎቶችን በማቅረብ እራሳቸውን እንዲችሉ መርዳት ነው።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ስብስቴ ነጋሲ ት/ቤት፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትንቢተ ኤርምያስ ት/ቤት፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወይራ ት/ቤት፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የማነ ብርሃን ት/ቤት እንዲሁም ት/ቤት መምጣት የማይችሉ በየቤታቸው ድጋፍ የሚያገኙ ልዩ ፍላጐት ያለባቸው ልጆች፤ ተቋሙ የሚረዳቸው ከ300 በላይ ልጆችን በሙያ በማሰልጠን እንዲሁም የሕክምናና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን በማድረግ ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡ ተገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

9 months ago