Logo
Getu Temesgen
የምድረ ገነት ሽረዉ አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀይዬ የአራት ጨዋታ እገዳ ተላለፈባቸዉ
#ethiopia | በምድረ ገነት ሽረዉ አሰልጣኝ ዳንኤል ፅሀይዬ ላይ የኢትዮጲያ ፕሪሚርሊግ አክሲዮን ማህበር ዉድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ የሶስት ጨዋታ እገዳ አስተላልፎባቸዋል።

አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀይዬ በአምስተኛዉ ሳምንት ቡድናቸዉ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገዉ ጨዋታ ላይ ያልተመዘገበ የቡድን አመራር በምክር መስጫዉ ላይ በመገኘቱ ካርድ የተመለከተ ሲሆን ያልተመዘገበዉ የቡድን አመራር ለፈፀመዉ ጥፋት ሶስት ጨዋታ ሲታገዱ እንድሁም በሶስት ጨዋታ ካርድ በመመልከታቸዉ ተጨማሪ አንድ ጨዋታ እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

በአምስተኛ ሳሞንት የኢትዮጲያ ፕሪሚርሊግ 53ቢጫ እና ሶስት ቀይ ካርዶች በዳኞች ሲመዘዙ 19 ግቦች ከመረብ አርፈዋል።

የካርድ ብዛቱ ከአራተኛ ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የሶስት ካርድ ጭማሪ ሲያሳይ የተቆጠሩት ጎሎችም በተመሳሳይ በሶስት ከፍ ብሏል።

የሲቢኢ የኢትዮጲያ ፕሪሚርሊግን ሲዳማ ቡና በ12 ነጥብ ሲመራ መቻል ፣ኢትዮኤሌክትሪክ እና ፋሲል ከነማ በእኩል 11 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠዉ ከሁለተኛ እሰከ አራተኛ ያለዉን ደረጃ ሲይዙ ወልዋሎ አድግራት ዩኒቨርሲቲ ፣ ወላይታ ድቻ ፣መቀሌ 70 እንደርታ እና ሀዲያ ሆሳዕና ሊጉ ግርጌ ላይ የተቀመጡ ቡድኖች ናቸዉ።

የሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት የቅዱስ ጊዮርጊሱ አቤል ያለዉ እና የሀዋሳ ከተማዉ ታዳጊ ያሬድ ብሩክ በእኩል አራት ግቦች እየመሩ ይገኛሉ።

የ6ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጲያ ፕሪሚርሊግ ጨዋታዎች ከኢትዮጲያ ዋንጫ ጨዋታዎች በኋላ ህዳር 11 የሚጀመሩ ይሆናል።

በ6ኛዉ ሳምንት ሀዋሳ የነበሩት 10 ቡድኖች ወደ አድስ አበባ ሲመጡ አድስ አበባ የነበሩት ደግሞ ወደ ሀዋሳ የሚያቀኑ ይሆናል ሲል ብስራት ኤፍ ኤም ዘግቧል።

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.