Logo
FIDEL POST NEWS
✈️ የቱርክ ወታደራዊ የጭነት አውሮፕላን ተከሰከሰ

አንድ የቱርክ C-130 ወታደራዊ የጭነት አውሮፕላን በአዘርባጃን እና በጆርጂያ ድንበር አቅራቢያ ተከስክሷል።

አውሮፕላኑ ከአዘርባጃን ወደ ቱርክ በመመለስ ላይ ነበር።

የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው፣ በአውሮፕላኑ ውስጥ ስንት የአውሮፕላን ሰራተኞች እንደነበሩ እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፣ ከአዘርባጃን እና ከጆርጂያ ባለስልጣናት ጋር በመተባበር የፍለጋ እና የማዳን ሥራ መጀመሩን ገልጿል።

የ C-130 የጭነት አውሮፕላን በቱርክ ጦር ለወታደራዊ ሠራተኞች እና ለሎጂስቲክስ ዕቃዎች ማመላለሻ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላል።

ቱርክ ከዚህች ሀገር ጋር ባላት መልካም ግንኙነት የተነሳ ለአዘርባጃን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ወታደራዊ ድጋፍ ስትሰጥ ቆይታለች።

ከተለቀቀው ቪዲዮ መረዳት እንደሚቻለው አውሮፕላኑ እየተሽከረከረ ከሰማይ ሲወድቅ፣ ሲወርድም ነጭ ጭስ ትቶ ይታያል። ቪዲዮው በቱርክ የግል ቻናል በሆነው ኤንቲቪ እና በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ተሰራጭቷል።
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.