የሀገሩን ጥሪ አልቀበልም ያለው የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጫዋች መነጋገሪያ ርዕስን ከፍቷል
#ethopia | ፌዴሪኮ ኪዬዛ የሀገሩን ጣልያን ብሄራዊ ቡድን ጥሪ አልቀበልም ማለቱን የአዙሪዎቹ አለቃ ጂናሪዮ ጋቱሶ በይፋ አሳውቋል።
ኮቬርሲያኖ በሚገኘው እና ብሄራዊ ቡድኑ በሚሰበሰብበት ቦታ ላይ መግለጫ የሰጠው የአዙሪዎቹ አለቃ እና የቀድሞ አስደናቂ ታጋይ አማካኝ መስመር ተጫዋች የሆነው ጂናሪዮ ጋቱሶ በስብስቁ ውስጥ ለምን ለፌዴሪኮ ኪዬዛ ጥሪ አልቀረበም ለሚለው ጥያቄ ጥሪው ደርሶታል ፤ በግል ጉዳዮች ምክንያት መካተት እንደማይፈልግ ነው የነገረን ሲሉ ተደምጠዋል።
ጣልያን ባለችበት ምድብ ኖርዌይ ምድቡን እየመራች እንደምትገኝ ይታወቃል። እስካሁን ከእንግሊዝ ውጪ ለ2026ቱ የአለም ዋንጫ ቲኬት መቁረጧን ያረጋገጠች ሀገር የለችም። ታዲያ የ4 ጊዜ የአለም ዋንጫ እንዲሁም የ2 ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋ ሀገር ጣልያን በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ላይ መሳተፏን ለማረጋገጥ ከሞልዶቫ እና ኖርዌይ ጋር ተጠባቂ ጨዋታዎቿን ታደርጋለች።
ለነዚህ ተጠባቂ ጨዋታዎች ደግሞ ቁልፍ የሚባሉ ተጫዋቾች ያስፈልጋሉ ፤ ኪዬዛም አንዱ ነው ፤ ሀገሩ በዚህ ወሳኝ ሰአት ስትፈልገው በግል ምክንያቶች በሚል ጥሪውን ያልተቀበለበት መንገድ በብዙዎች ተጫዋቹ ትዝብት ውስጥ እንዲገቃ አድርጎታል።
አሰልጣኝ ጋቱሶ ታክቲካል ወይም physical assessment ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ በመጥቀስ ተጫዋቹ በራሱ ፍላጎት ጥሪውን እንዳልተቀበለ ተናግሯል ፤ እንግዲህ ተጫዋቾች የሚሉትን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለንም ሲልም አያይዞ ሀሳቡን ሰጥቷል።
ጣልያን በአለም ዋንጫ መሳተፏን የምታረጋግጥ ከሆነ ኪዬዛ ጥሪ ይቀርብለታል የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነወ። በርካታ የእግርኳስ ቤተሰቦች በክለቡ ደረጃ እንኳን የመሰለፍ እድልን ከስንት አንድ ጊዜ የሚያገኝ ተጫዋች የትኛውም የግል ምክንያት ቢኖረው ጥሪውን የመቀበል ግዴታ ነበረበት የሚል ሀሳብ እንዲያነሱ እያስገደዳቸው ይገኛል። ሀገሩ ስትፈልገው ካልተገኘ ፤ ሀገሩ ለአለም ዋንጫ ስታልፍ ጥሪ ሊደርሰው እንደማይገባ ሀሳቦችን እያሰፈሩ ይገኛሉ ሲል መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

9 months ago