Logo
Getu Temesgen
ፑቲን አሜሪካ የኒውክሌር ሙከራዋን ከቀጠለች ሩሲያ የአፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ ተናገሩ
#ethiopia | ዩናይትድ ስቴትስ ከአሥርተ ዓመታት ቆይታ በኋላ የራሷን የኒውክሌር ሙከራ እንድትቀጥል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትእዛዝ መስጠታቸውን ተከትሎ የሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ለክሬምሊን ከፍተኛ ባለሥልጣናት የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሙከራን እንደገና ለመጀመር የውሳኔ ሃሳቦችን እንዲያዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። የሩስያ መሪ ለፀጥታው ምክር ቤት እንደተናገሩት ዩናይትድ ስቴትስ ወይም ማንኛውም የኑክሌር ሙከራ ክልከላ ስምምነት (ሲቲቢቲ) ፈራሚ ሀገራት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራዎችን ቢያካሂድ "ሩሲያ አጸፋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ግዴታ አለባት" ማለታቸውን ክሬምሊን ገልጿል።

"በዚህ ረገድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን፣ የመከላከያ ሚኒስቴርን፣ የልዩ አገልግሎትን እና ተዛማጅ የሲቪል ኤጀንሲዎችን በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለመሰብሰብ፣ በፀጥታው ምክር ቤት እንዲተነተን እና ለኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራዎች ዝግጅት ላይ ያተኮሩ የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ የተቀናጁ ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ የተቻለውን ሁሉ እንዲያደርጉ አዝዣለሁ" ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።እ.ኤ.አ. በ 1991 ከሶቪየት ህብረት ውድቀት በኋላ ሞስኮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራዎችን አላደረገችም ። ነገር ግን ከአለም ትልቁ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውዝግብ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየጨመረ መጥቷል።

ትራምፕ በፑቲን ላይ ያላቸው ብስጭት የመጣው ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ የጀመረችውን ጦርነት የማቆም አዝማሚያ አለማሳየቷን ተከትሎ ነው።የዩናይትድ ስቴትስ መሪ በጥቅምት ወር በሃንጋሪ ከፑቲን ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ስብሰባ ሰርዘዋል። ከአንድ ቀን በኋላ በሁለት ዋና ዋና የሩሲያ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።ትራምፕ በጥር ወር ወደ ኋይት ሀውስ ከተመለሱ በኋላ ይህ የመጀመሪያው እርምጃቸው ነው።ትራምፕ በመቀጠል የመከላከያ ዲፓርትመንት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራን ከሌሎች ኑክሌር የታጠቁ ሃይሎች ጋር “በእኩልነት” እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል ሲል ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.