የሦስቱን ኪሞች ‘ስመ-ርዕሰ መስተዳድር’ ያገለገሉት አንጋፋ ባለስልጣን በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያ ‘ስመ-ርዕሰ መስተዳድር’ (Nominal Head of State) በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት እና የሀገሪቱን ሶስቱን መሪዎች ኪም ኢል ሱንግ፣ ልጃቸው ኪም ጆንግ ኢል እና የልጅ ልጃቸው ኪም ጆንግ ኡንን በታማኝነት ያገለገሉት አንጋፋው ባለስልጣን በ97 ዓመታቸው ማረፋቸውን የሀገሪቱ የመንግስት ሚዲያዎች አስታወቁ።
ሟቹ ባለስልጣን የኮሪያን ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ የህዝብ ምክር ቤት ፕሬዚዲየም ፕሬዚዳንት በመሆን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ ይህ ስልጣን በውጭ ሀገራት የሰሜን ኮሪያን ወክሎ የሚንቀሳቀስ ‘የስም ርዕሰ መስተዳድር’ ተደርጎ ይወሰዳል።
በሰሜን ኮሪያ ውስጥ እውነተኛው ስልጣን ሁልጊዜም በኪም ቤተሰብ ውስጥ ቢሆንም፣ ሟቹ ባለስልጣን በሀገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው እና ከኪም ኢል ሱንግ ዘመን ጀምሮ እስከ ኪም ጆንግ ኡን ዘመን ድረስ በከፍተኛ የመንግስት እርከኖች ውስጥ የቆዩ ብርቅዬ ምስክር ነበሩ ተብሏል።
የሞት መንስኤ በይፋ ባይገለጽም፣ የሰሜን ኮሪያ ሚዲያ የሟቹን “ለፓርቲ እና ለመሪዎች ያሳዩትን ታማኝነት” አድንቆ፣ ሀገሪቱ ታላቅ አርበኛ ማጣቷን ዘግቧል።

9 months ago