Logo
Getu Temesgen
ቀይ ባህር የኢትዮጵያ መልህቅ ፣የዜጎች ሚና ከብሔራዊ ጥቅም ዓይን
#ethiopia | አሁንም መነሻችን በተለይ በእኔ ዘመን ላሉ የትውልዱ አካል እና በትናንትና ሀቲት ላይ ሳይኖሩ ለአገራቸው ቀና ሀሳብ ላላቸው በውስጣቸው የአገር ፍቅር ንዳድ ሌት ከቀን ለሚሳስባቸው ለእኔ ዘመን ትውልድ አካል(As a member of this generation)ይህ እይታዬ (perspective )እንዲሆንልልኝ እመኛለሁ ።

ትናንት የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሲገነባ በቀንነት ልማትን እና እድገት ሲደገፉ የነበሩ ዜጎች ይደርስባቸው የነበረው ያልተገባ አስተያየት ቆም ብሎ በማስተዋል ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ አባው ሳይረፍድብን በክቡር የኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ በህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ያቀረቡትን ሀሳብ በመመልከት እንደ ዘመኑ የትውልድ አካል በትንሹ ከቀሰምኩት (Global studies and international relations ) የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት አኳያ የግል ምልከታዬን አካፍላለሁ ።

የኢትዮጵያ ወደብ አልባነት (Landlocked status) ለኢኮኖሚያዊና ለፀጥታ ችግሮች ዋነኛ መንስዔ መሆኑን በማመን፣ቀይ ባህርን በሰላማዊ መንገድ ማግኘት የሀገር ህልውና ጉዳይ ነው። ይህን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ መሻት ለማሳካት ዜጎች የሚከተሉትን ሚናዎች መጫወት ይገባቸዋል።በሀገራዊ መግባባት እና አንድነት ላይ መስራት (የውስጥ መደመር) ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር የሚጀምረው በጠንካራ የውስጥ አንድነት ነው፥ዜጎች በሁሉም ልዩነታቸው "በመደመር" መንፈስ በመተባበር፣ የጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎችን መደገፍ አለባቸው።

የዜጎች ሚና በተለያዬ ሀሳቦች ያለመከፋፈል በቀይ ባህር ዙሪያ ያሉ ጥያቄዎችን ከፓርቲና ከማንነት ፖለቲካ በላይ በማስቀደም፣ለብሔራዊ ዓላማ በጋራ መቆም ይገባል።አሉባልታዎችን መዋጋት በዘመነ ድህረ እውነት ( misleading content deliberately spread to deceive people ) በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ዙሪያ የሚነሱ የውስጥና የውጭ የጥላቻና የጥፋት ወሬዎችን በእውነት ላይ በተመሠረተ ግንዛቤ በማሸነፍ በሁሉም አውዶች ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዙሪያ ድምጽ መሆን (የውጭ መደመር) ኢትዮጵያ የምትመርጠው መንገድ የኃይል ሳይሆን የሰላማዊ ድርድርና ትብብር መሆኑን ለዓለም ማሳመን(Collaboration,not confrontation)። የዲያስፖራው ሚና በውጭ ሀገር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን( ከምናባዊ ሀገር )በመውጣት የአገራቸውን የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፍ ሕጎችንና ምክንያቶችን መሠረት በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ማስረዳት፣ የሎቢ( Looby )ሥራ መሥራት እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን መደገፍ ይገባቸዋል ።ይህ ጊዜ እንደትናንቱ እንዳይቆጨን በአስታውሎት ማጤን ያስፈልጋል ።

እውቀትን ማጋራት(Dissemination, knowledge transfer, communication, and education) የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ፣ምሁራን፣ የሕግ ባለሙያዎችና የታሪክ ተመራማሪዎች ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መብቷን የሚያረጋግጡ ታሪካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ዓለም አቀፍ የሕግ መረጃዎችን አጥንተው ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ( International community) በማቅረብ ለህዝባቸው ያላቸውን ወገንተኝነት ማሳየት አለባቸው ።

ለቀይ ባህር ተጋሪነት ጥያቄ መሠረቱ ጠንካራ ኢኮኖሚና ብሔራዊ አቅም ነው። ወደብ ማግኘት ዋናው ግብ አይደለም፤ ነገር ግን ወደቡን በብቃት መጠቀም መቻል ነው።ምርታማነትን ማሳደግ እያንዳንዱ ዜጋ በየሥራው ምርታማነትን በመጨመር የሀገርን ኢኮኖሚ ማጠናከር ይኖርበታል።ጠንካራ ኢኮኖሚ የዲፕሎማሲው አውራ ክንድ ነው በእጥፍ እያደግን እና እየተለወጥን ስንመጣ በኢንቨስትመንት አቅም እና እድል የኢትዮጵያ ዲያስፖራና ባለሀብቶች (የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ) ወደፊት ለሚከፈቱ የሎጂስቲክስና ወደብ ልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስና እውቀት በማፍሰስ የባህር በርን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይችላሉ ።

ለቀጣናዊ ሰላም መስበክ (የሰላም መደመር) ቀይ ባህር መልህቅ እንዲሆን የሚቻለው ቀጠናው ሲረጋጋ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ በልዩ ልዩ መንገድ ስለ ሰላም አስፈላጊነት እና ጥቅም በሚገባ መግለጥ ይገባል ከእያንዳነዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ ይጠበቃል ።

አዎንታዊ ትርክት መፍጠር ( Pragmatic narratives-self-interests, national aspirations, and global complex interdependence) ኢትዮጵያ ወደብ የምትፈልገው ጎረቤቶቿን ለመጉዳት ሳይሆን የሁሉንም ወገን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር መሆኑን የሚያሳይ አዎንታዊ መልእክት ማስተላለፍ፤ቀይ ባህር የኢትዮጵያ መልህቅ እንዲሆን የዜጎች ተግባር የተናጠል ትርፍን ትቶ ለጋራ ብሔራዊ ጥቅም በጠንካራ የ"መደመር" መንፈስ መቆም ነው።

ይህ የአስተሳሰብ ለውጥ ወደ አንድነት፣ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ እና ቀጣናዊ ሰላም የሚያደርስ ዘላቂ የሀገር ህልውና ዋስትና በመሆኑ ዛሬን ከተጉበት ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ዘላቂ ውጤት በትብብር መስራት ያስፈልጋል ። በቀጣይነትም ከዚህ አጀንዳ እና ሀገራዊ ጥቅም አንፃር የሚኖረኝን መረዳት አካፍላለሁ ።

በሀብታሙ ደባሱ አዲሱ

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.