ትራምፕ ደቡብ ኮሪያ ከመድረሳቸው በፊት ሰሜን ኮሪያ ተቃውሞዋን ለማሳየት ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ጉባኤ በደቡብ ኮሪያ እንደደረሱ ወዲያውኑ፣ ሰሜን ኮሪያ ስትራቴጂካዊ የክሩዝ ሚሳኤሎችን ከባሕር ወደ ምድር የማስወንጨፍ ሙከራ ማድረጓን የመንግስት ሚዲያዋ ኬሲኤንኤ (KCNA) ዘገበ።
ሙከራው የተካሄደው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በ3:00 ሰዓት (በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር) አካባቢ ሲሆን፣ ሚሳኤሎቹ የተተኮሱት ከኮሪያ ልሳነ ምድር ምዕራባዊ ክፍል በሚገኘው ቢጫ ባህር (Yellow Sea) ውስጥ ነው። የሰሜን ኮሪያ የመንግስት ሚዲያ እንዳለው፣ ሚሳኤሎቹ በተወሰነላቸው መስመር ላይ ከሁለት ሰዓት በላይ (ከ7,800 ሰከንድ በላይ) በአየር ላይ ከበረሩ በኋላ ኢላማቸውን በትክክል መምታት ችለዋል። የደቡብ ኮሪያ ተንታኞች እንደሚገምቱት፣ እነዚህ ሚሳኤሎች እስከ 1,500 ኪሎ ሜትር የመምታት አቅም አላቸው።
ፒዮንግያንግ ይህንን የጦር መሳሪያ ሙከራ ያከናወነችው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ የጎበኙበትን ጊዜ በመምረጥ የግልጽ ተቃውሞና ንቀት ለማሳየት ነው። የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን ፓክ ጆንግ ቾን እንደተናገሩት፣ ሙከራው የተካሄደው የሀገሪቱን የጦርነት መከላከያ አቅም የሚያሳድገውን "የኑክሌር ኃይል" በተግባር ላይ በማዋል፣ በጠላቶች ላይ ወታደራዊ ችሎታን ለማሳየት እና አስተማማኝነታቸውን ለመፈተሽ ነው። ይህ ተግባር በ2019 ዓ.ም በትራምፕ እና በኪም ጆንግ ኡን መካከል የተጀመረው የኒውክሌር ድርድር ከተበተነ በኋላ በዋሽንግተን ላይ የተሰነዘረ ሌላ ወታደራዊ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የደቡብ ኮሪያ የጋራ ኤታማዦር ሹሞች (JCS) ሚሳኤል ማስወንጨፉን መለየታቸውን አረጋግጠው፣ ዝርዝር ትንተና በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን ከጃፓን ወደ ደቡብ ኮሪያ በሚያደርጉት የበረራ ጉዞ ላይ ሳሉ ስለ ማስወንጨፉ ተጠይቀው አቅልለው ተመልክተዉታል። "እሱ (ኪም ጆንግ ኡን) ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሚሳኤሎችን ሲያስወንጭፍ ቆይቷል አይደል?" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። አክለውም፣ ኪም ጆንግ ኡንን ለመገናኘት አሁንም ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በአጠቃላይ፣ የሰሜን ኮሪያ ድርጊት አሜሪካ እና ቻይና በፓስፊክ ክልል የንግድ እና የደኅንነት ውጥረቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን በሚያደርጉበት ወቅት መፈጸሙ፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የፒዮንግያንግን ጉልህ ስፍራ እንዲይዝ ማድረጉን ታዛቢዎች ይገልጻሉ ሲል የዘገበው መናኸሪያ ኤፍ ኤም ነው።

9 months ago