ለሎተሪ አሸናፊዎች ሽልማት ተበረከተ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሎሽንስ ጋር በመሆን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አሸናፊዎችን በታላቅ ስነ-ስርዓት ሸለመ፡፡
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ለ65 ዓመታት ያህል ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የደስታ እንዲሁም የለውጥና የዕድል ምንጭ ሆኖ አገልግሏል::
የሽልማት መጠኑን በ50 ሺህ ብር አሀዱ ብሎ ጀምሮ ዛሬ ላይ ሽልማቱን በሚሊዮን አሳድጎ በርካቶችን በሽልማት ያንበሸበሸ ትልቅ ተቋም ነው፡፡
አሁን ላይ ይህ ተቋም ከዘመኑ ጋር እኩል በመራመድ በቴክኖሎጂው እየታገዘ ሎተሪን በወረቀት ብቻ ሳይሆን በዲጂታል አማራጭበማቅረብ ደንበኞቹ በየትኛውም ቦታ ሆነው በቀላሉ ዕድላቸውን እንዲሞክሩ አስችሏል፡፡
ዕድል ከቴክኖሎጂ ጋር መተሳሰርን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር ባሳለፍነው ዓመት አራት የሎተሪ ዘመቻን በዲጂታል በመሽጥ በስኬት አጠናቋል፡፡ ይህ የዲጂታል ሽያጭ ደማቅ የሆኑ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዐቶችን እና የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት የሳቡ የሽልማት መርሃግብሮችን በማከናወን ግልፅነትና ታአማኒነትን ከማስፈን ባሻገር የኦንላይን ደንበኞች አባላት ቁጥር ወደ አንድ ሚሊዮን እንዲደርስ አስችሏል፡፡
ለሁለት ወራት ያህል በዲጂታል እና በወረቀት ሲሸጥ የቆየው የ"እንቁጣጣሽ ሎተሪ" የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት በስኬት ከተከናወነ በኋላ ዛሬ ለዕድለኞች የሚከተሉት ሽልማቶች ተሰጥተዋል፦
የገንዘብ ሽልማቶች በዲጂታል እና በወረቀት ለገዙ ፦ 👉 20 ሚሊዮን ብር ወይዘሮ ጌጤነሽ ብሩ
👉 10 ሚሊዮን ብር ወጣት አለሙ አማረ
👉 2.5 ሚሊዮን ብር አቶ በረከት ቢሆነኝ
👉 2.5 ሚሊዮን ብር አቶ በረከት ቢሆነኝ
👉 2.5 ሚሊዮን ብር አቶ ሀይሉ ተረዳ
👉 250ሺ ብር አቶ አስማረ መኮንን
እንቁጣጣሽ ሎተሪን በዲጂታል ለቆረጡ ብቻ ልዩ የቦነስ ሽልማት
👉 አቶ አስማረ ዱፋ የBYD ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ
👉 አቶ ኦልያድ ደሜ የኤሌክትሪክ ባጃጅ ለዕድለኞች ተሸልመዋል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በቀጣይ በ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ በ100 ብር ከ125 ሚሊዮን ብር በላይ ለሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን በየሳምንቱ ቅዳሜ አንድ ሚሊዮን ብር የቦነስ ሽልማት መዘጋጀቱን ተገልጿል።
በተጨማሪም ዕለታዊ ሎተሪ በ5 ብር እስከ 25,000 ብር በየቀኑ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን ልዩ ዕድል ሎተሪ በ100 እስከ 10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ሲሆን ዕጣው ህዳር 1 እንደሚወጣ ተገልጿል።
ሁሉንም በቴሌብር እና በ ethiolottery.et ላይ ያገኙታል!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳዲስ የዕድል አማራጮችን ለህብረተሰቡ ማቅረብ እንደሚቀጥል በመግለፀ አሸናፊዎቹን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

10 months ago