Logo
YenetaTube
በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር።
ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት።
ትውልዷ ከእስክንድርያ፣ ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። በአስራ ሁለት ዓመቷ የሰው ሁሉ ጠላት ሰይጣን ሸንግሎ አሳታት፡፡ በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ፡፡ ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና። ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በመርከብ ተሳፈረች።
ባለ መርከቦችም የጉዞ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው፡፡ የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወዳለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም።

ይህን ጊዜ የረከሰ ስራዋን አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ እግዚአብሔር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስዕል አየች። በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጂያቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት። ወደ ቤተ ክርስቲያን በገባችም ጊዜ የበዓሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኃላ እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ፣ እያለቀሰች ስለነፍሰዋ ተማጸነች፡፡ የለመኗትን የማትነሳ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእልም ወደ ዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ እረፍትንና ድኀነትን ታገኛለሽ የሚል ቃል ወጣ።

ወጥታ ስትሄድም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ዲናር ሰጣትና ሕብስት ገዛችበት፡፡ የዮርዳኖስንም ወንዝ ተሻግራ በበረሀው ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በጸሎትና በስግደት አርባ ሰባት ዓመት ኖረች፡፡ ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር። እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች የገዛችውን ሕብስትም ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለትና ሶስት ቀናት እየጾመች ጥቂት ሕብስት ትቀምስ ነበር፡፡ ባለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች። ከአርባ ሰባት ዓመት በኋላ ቅዱስ አባ ዞሲማ እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ወደዚያች በረሀ መጣ። ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚጽናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው። በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሀት መሰለችው በጸለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት።

ግብጻዊቷ ማርያም ነገር ግን ከእርሱ ሸሸች ከኃላዋ በመሮጥም ተከተላት። እርሷም በስሙ ጠርታ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ አለችው። በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ እርሱ ካህን ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት በላዩዋም ጸለየላት። በብዙ ልመናም ገድሏን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። በቀጣዩ ዓመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው አምጥቶም ጸልዮ አቀበላት። በሁለተኛው ዓመት ወደ ዮርዳኖስ በረሀ ሲመጣ ግብጻዊቷ ቅድስት ማርያም ሙታ አገኛት፣ አንበሳ ጉድጓዷን ቆፍሮለትም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት። ገዳማውያን የዓለምን ከንቱነት ተረድተው ትተዋት ሔደዋል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.