የ65 አመት አዛውንት በ23 ዓመት እስራት ተቀጣ
#ethiopia | በሲዳማ ክልል በይጋለም ከተማ የ12 አመት ታዳጊን የ65 አመቱ አዛውንት አቶ ካሳሁን ናስር አስገድዶ መድፈሩ የአቃቤ ህግ ማስረጀ ያስረዳል ።
ግለሰቡ አስገድዶ ከመድፈሩም በላይ በደሙ የHIV ቫይረስ እንዳለበት እያወቀ እንዲሁም ለ14 አመታት የጸረ ኤች አይ ቪ መዳኒት ይጠቀም እንደነበር ይርጋለም ሆስፒታል ያረጋገጠ መሆኑ ተገልጿል ።
ጉዳዩ በከተማው መጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት እየታየ ቆይቶ በጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ወንጀል ችሎት ግለሰቡ ጥፋተኛ ነው ተብሏል ።
ግለሰቡ ለቅጣት ማቅለያ ተጠይቆ የHIV ቫይረስ በደሙ እንደሚገኝ የስኳር እና የደም ግፊት ታማሚ መሆኑን የሚገልጽ የህክምና ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ እንዲሁም ቤተሰቡን እና ህጻናት ልጆቹን የሚያስተዳድረው ሊስትሮ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ በጥፋት ማቅለያነት ለፍርድቤቱ አቅርቦ በመጨረሻም ፍርድቤቱ እሱን ያስተምራል ለሌሎቹ ትህምርት እንዲሆን 23 አመት ከ6 ወር እንዲቀጣ ፈርዶበታል።
ይህ እንዲህ እንዳለ በወቅቱ ህጻኗ እንደተደፈረች የድንገተኛ የኤች አይቪ ቫይረስ መከላከያ በይርጋለም ሆስፒታል (ፕሮፍላክሲስ) የተሰጣት ሲሆን በዚህ ግዜ ተመርምራ ከቫይረሱ ነጻ መሆኗ ተረጋግጧል ሲል የዘገበው ብስራት ኤፍ ኤም ነው ።

10 months ago